የኩላሊት ዋና ተግባር ከሰውነት ውስጥ አላስፈላጊ ግብዐቶችን በማስወገድ ደምን ማጣራት ነው። ኩላሊት ከዚህ በተጨማሪም አላስፈላጊ ውሃን ፣ ማዕድናት እና ውህዶች/ ኬሚካሎች ከሰውነት በማስወገድ እንዲሁም እንደ ሶድየም ፣ ፖታሲየም ፣ ካልሲየም ፣ ፎስፈረስ እና ባይካርቦኔት ያሉ ማዕድናትን በመቆጣጠር ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
ሥር በሰደደ የኩላሊት ህመም የሚሰቃዩ ሕመምተኞች በሰውነት ውስጥ ያሉ ፈሳሾች እና ማእድናትን በመቆጣጠር ላይ ከፍተኛ እክል ሊገጥም ይችላል። በዚህ ምክንያት አግባብ ያለው የውሃ(ፈሳሽ) አወሳሰድ እንዲሁም መደበኛ የገበታ ጨው ወይም ፖታስየም መውሰድ እንኳን በሰውነት የፈሳሽ እና ማእድናትን ሚዛን ላይ መዛባት ሊያስከትል ይችላል።
ጉዳት በደረሰበት ኩላሊት ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ እና የፈሳሽ እንዲሁም የማእድናትን ሚዛን መዛባትን ለመቆጣጠር ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመምተኞች የአመጋገብ ስርአት የህክምና ባለሞያ ባሰፈረላቸው መመሪያ መሰረት ማሻሻል ይኖርባቸዋል። ሥር ለሰደደ የኩላሊት ታካሚዎች ምንም ዓይነት ቋሚ የምግብ መመሪያ የለም ፤ እያንዳንዱ ሕመምተኛ ባለበት የጤና ሁኔታ ፣ እንዲሁም ባለበት የኩላሊት የጉዳት ደረጃ ላይ በመመርኮዝ የተለያየ የአመጋገብ ምክር ይሰጣል።
1. ከፍተኛ የሃይል መጠን ያላቸውን ምግቦች መውሰድ
ሰውነታችን ለዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች፣ የሙቀት መጠንን እንዲሁም እድገት እና የሰውነት ክብደትን ለመጠበቅ በቂ የሆነ ካሎሪ ይፈልጋል። በዋነኝነት ሃይል የሚገኘው ከሃይል ሰጪ ምግቦች እና ከቅባቶች ነው።
ሥር የሰደደ ኩላሊት ህመምተኞች መደበኛ የሃይል ፍላጎት በቀን ከ 35-40 ኪሎ.ካሎሪ/ ኪ.ግ. ሲሆን ይህ በቂ ሳይሆን ሲገኝ ሰውነታችን ሃይል ለማቅረብ ገንቢ ምግብን (ፕሮቲንን) ይጠቀማል። ይህ ከፍ ያለ ፕሮቲንን (ገንቢ ምግብን ለሃይል) መጠቀም እንደ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና ከፍተኛ ጎጂ የሆኑ የቆሻሻ ምርቶችን ያስከትላል። ስለሆነም ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመምተኞች በቂ የሃይል መጠን ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው። እንደ ታካሚው ወቅታዊ ክብደት ሳይሆን የበሽተኛውን ተስማሚ ክብደት በመጠቀም የካሎሪ ፍላጎቱን ማስላት አስፈላጊ ነው።
ሥር በሰደደ የኩላሊት ህመምተኞች የፈሳሽ አወሳሰድን በተመለከተ ምን ጥንቃቄ መውሰድ አለባቸው?
ኩላሊቶች በሰውነት ውስጥ ከመጠን በላይ ፈሳሽ እንደ ሽንት በማስወገድ ትክክለኛውን የውሃ መጠን በመጠበቅ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። በ ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመምተኞች ላይ የኩላሊት ሥራ እየተዳከመ ይሄዳል ፣ ብዙውን ጊዜ የሽንት መጠኑም ይቀንሳል። መጠኑ የቀነሰ የሽንት መጠን በሰውነት ውስጥ ፈሳሽ እንዲከማች ያደርጋል ፤ ይህም የፊት እብጠት ፣ የእግሮች እና የእጆች እብጠት እና የደም ግፊት ያስከትላል። በሳንባዎች ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት (ፐልሞናሪ ኢዴማ ተብሎ የሚጠራ ሁኔታ) እብጠት እና መጨናነቅ በመፍጠር የትንፋሽ እጥረት እና የመተንፈስ ችግር ያስከትላል። ይህ ካልተቆጣጠሩት ለሕይወት አስጊ ሊሆን ይችላል።
በሰውነት ውስጥ ከመጠን በላይ ፈሳሽ መኖር ይባላል። የእግር እብጠት ፣ በሆድ ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት ፣ የትንፋሽ ማጠር እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ክብደት መጨመር በሰውነት ውስጥ ከመጠን ያለፈ ፈሳሽ መኖሩን የሚጠቁሙ ፍንጮች ናቸው።
ፈሳሽ ከመጠን በላይ መጠራቀም ወይም ጉድለትን ለማስወገድ የፈሳሽ መጠን መመዝገብ እና በዶክተሩ ምክር መሠረት ክትትል መደረግ አለበት።
ለእያንዳንዱ የኩላሊት ህመምተኛ የሚፈቀደው ፈሳሽ መጠን የእያንዳንዱ ህመምተኛ የሽንት መጠን እና የሰውነት የፈሳሽ ሁኔታ ላይ መሰረት ያደረገ ስለሚሆን ለእያንዳንዱ የሚመከረው የፈሳሽ መጠን ሊለያይ ይችላል።
ፈሳሽ አወሳሰድን መገደብ ከባድ ነው ፤ ነገር ግን እነዚህ ምክሮች ይረዱዎታል-
በሶዲየም የበለጸጉ ምግቦች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ
የኩላሊት ህመምተኞች በአመጋገብ ውስጥ ፖታስየም እንዲገድቡ ለምን ይመከራሉ?
የጡንቻዎች ፣ የነርቮች ትክክለኛ አሠራር እና የልብ ምት በመደበኛነት እንዲመታ ማድረግ የፖታስየም ማዕድን በሰውነት ውስጥ አስፈላጊ ተግባራቶች ናቸው። በሰውነት ውስጥ ያለው የፖታስየም መጠን ሚዛናዊነት ፖታስየም የያዙ ምግቦችን በመመገብ እና ከመጠን በላይ የፖታስየምን በሽንት ውስጥ በማስወገድ ይጠበቃል። ሥር በሰደደ የኩላሊት በሽታ ህመምተኞች ፖታሲየምን ከሽንት ውስጥ ማስወገድ ደካማ ስለሆነ በደም ውስጥ ያለው ፖታስየም በከፍተኛ መጠን ሊጠራቀም ይችላል። ይህ ሁኔታ ሃይፐርካሌሚያ ተብሎ ይጠራል።
የሃይፐርካሌሚያ መከሰት የፔሪቶኒያል ዲያሊሲስ የሚያደርጉ ሕመምተኞች ከሄሞዲያሊሲስ ላይ ካሉት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ነው። ይህ የሆነው በፔሪቶኒያል ዲያሊሲስ ጊዜ ዲያሊሲሱ ቀጣይነት ያለው ሲሆን በሄሞዲያሊሲስ ጊዜ ግን አልፎ አልፎ ይደረጋል።
ከፍተኛ የፖታስየም መጠን ከፍተኛ የጡንቻ ድክመት ወይም አደገኛ ሊሆን የሚችል ያልተለመደ የልብ ምት ሊያስከትል ይችላል። ፖታስየም በጣም ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ ልብ ባልታሰበ ሁኔታ መምታት ማቆም እና ድንገተኛ ሞት ያስከትላል። ከፍተኛ የፖታስየም መጠን በግልጽ የሚታዩ ክስተቶች ወይም ምልክቶች ሳይኖሩ ለሕይወት አስጊ ሊሆን ይችላል ስለዚህ ዝምተኛ ገዳይ በመባል ይታወቃል። የፖታስየም አስከፊ ጉዳቶችን ለማስወገድ የኩላሊት ህመምተኞች በአመጋገብ ውስጥ ፖታስየም እንዲገደብ ይመከራል።
ከፍተኛ ፎስፈረስ የያዙ ምግቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ
ሥር በሰደደ የኩላሊት ህመም ህመምተኞች በቅድመ-ዲያሊሲስ ወቅት በዝቅተኛ የምግብ ፍላጎት እና የኩላሊት ህመም መባባስን ለማዘግየት ሲባል ከመጠን በላይ የተከለከለ አመጋገብ በአጠቃላይ በቂ ያልሆነ የቪታሚኖች አቅርቦት ይኖራቸዋል። የተወሰኑ ቫይታሚኖች - በተለይም በውሃ ውስጥ የሚሟሙ ቫይታሚኖች እንደ ቫይታሚን ቢ ፣ ቫይታሚን ሲ እና ፎሊክ አሲድ - በዲያሊሲስ ወቅት ይጠፋሉ።
የእነዚህ ቫይታሚኖች አጠር አመጋገብ ወይም የቪታሚኖች መጓደልን ለማካካስ የኩላሊት ህመምተኞች ብዙውን ጊዜ በውሃ ውስጥ የሚሟሟ ቫይታሚኖችን እና ተጨማሪ ጥቃቅን ንጥረነገሮች ያስፈልጓቸዋል። ከፍተኛ የፋይበር መጠን ሥር በሰደደ የኩላሊት በሽታ ህመምተኞች ጠቃሚ ነው። ስለሆነምታካሚዎች በቪታሚን የበለፀጉ ትኩስ አትክልቶችን እና ፍራፍሬዎችን የበለጠ እንዲወስዱ፤ እንዲሁም ከፍተኛ መጠን ያለው የፖታስየም ይዘት ያላቸውን ምግቦች እንዳይወስዱ ይመከራል።
1. የውሃ እና ፈሳሽ ምግብ አወሳሰድ፡- ፈሳሽ አወሳሰድ በሐኪሙ ምክር መሠረት ውስን መሆን አለበት። ዕለታዊ ክብደት ተጠብቆ መቆየት አለበት። በክብደቱ ውስጥ ማንኛውም ተገቢ ያልሆነ ጭማሬ ከአስፈላጊ ከተስተዋለ ከተገቢዉ በላይ ፈሳሽ መውሰድን ሊያመለክት ይችላል።
2. ሃይል ሰጪ ምግብ /ካርቦሃይድሬት፡- ሰውነት በቂ ሃይል ማግኘቱን ለማረጋገጥ ኩላሊት በሽታ ህመምተኞች ተያያTh የስኳር ህመምተኛ ካልሆኑ ስኳር ወይም ግሉኮስ የያዘ ምግብ መውሰድ ይችላሉ።
3. ገንቢ ምግብ / ፕሮቲን፡ ሥጋ ፣ ወተት ፣ እህሎች ፣ ጥራጥሬዎች ፣ እንቁላል እና ዶሮ ዋናዎቹ የገንቢ ምግብ ምንጮች ናቸው። በኩላሊት የደም ማጣራት ህክምና (ዲያሊሲስ) ያልጀመሩ የኩላሊት ህመምተኞች አመጋገብ የገንቢ ምግብ /ፕሮቲንን ወደ <0.8 ግራም / ኪግ አካል ክብደት / ቀን እንዲወስን ይመከራል። በኩላሊት የደም ማጣራት ህክምና (ዲያሊሲስ) የጀመሩ ህሙማን የአመጋገብ ምጣኔን ከ1-1.2 ግራም / ኪግ የሰውነት ክብደት / ቀን ከፍ ማድረግ ይቻላል።
የፔሪቶኒየል የደም ማጣራት ህክምና /ዳያሊስስን የሚያካሂዱ ታካሚዎች በየቀኑ እስከ 1.5 ግራም / ኪግ/በቀን የሰውነት ክብደት ወሳኝ የገንቢ ምግብ ያስፈልጋቸዋል። የእንስሳት ተዋጽ ኦ ገንቢ ምግብ ሁሉንም አስፈላጊ አሚኖ አሲዶች ይይዛሉ (ስለሆነም የተሟሉ የገንቢ ምግብ ይባላሉ ወይም ከፍተኛ ባዮሎጂያዊ እሴት ያላቸው ይባላሉ) እንዲሁም ተስማሚ ይሆናሉ ፤ ነገር ግን ከእነዚህ የገንቢ ምግብ /ፕሮቲኖች የደም ማጣራት ህክምና /ዲያሊሲስ ያልጀመሩ ታካሚዎች የሚመገቡትን መጠን መቀነስ አለባቸው ምክንያቱም ለሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም መባባስን እና መፋጠን መክንያት ይሆናል።
4. ቅባት- ቅባት ጥሩ የካሎሪ ምንጭ እንደመሆናቸው መጠን እንደ ኃይል ምንጭ ሊወሰዱ ይችላሉ። ሞኖአንሳቹሬትድ እና ፖሊአንሳቹሬትድ ቅባቶችን በወይራ ዘይት ፣ በሱፍ አበባ ዘይት ፣ በካኖላ ዘይት ወይም በአኩሪ አተር ዘይት መልክ ውስን በሆነ መጠን ሊወሰዱ ይችላል። በእንስሳት ስብ ውስጥ የሚገኙ የተሟሉ ቅባቶችን ከመጠቀም ይቆጠቡ።
5. ጨው- አብዛኛዎቹ ህመምተኞች አነስተኛ የጨው ምግብ እንዲመገቡ ይመከራሉ። "ጨው ያልተጨመረበት" አመጋገብን ማክበር ጥሩ ነው። ዝቅተኛ የሶዲየም ምግቦች በውስጣቸው የያዙት የጨው መተኪዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ፖታስየም አለመያዛቸውን ያረጋግጡ። የምግብ ስያሜዎችን እንደ ሶዲየም ባይካርቦኔት ያሉ ሶዲየም ለያዙ ሌሎች ምግቦች ይፈትሹና እንደ(ቤኪንግ ዱቄት) ያሉትን ያስወግዱ።
6. እህሎች- እንደ ጠፍጣፋ ሩዝ ያሉ ወይም ሌሎች የሩዝ ምርቶች ሊወሰዱ ይችላሉ። የአንድ ዓይነት ጣዕም መሰላቸትን ለማስወገድ አንድ ሰው እንደ ስንዴ ፣ ሩዝ ፣ ሳጎ ፣ ሰሞሊና ፣ ዱቄት ያሉ የተለያዩ የእህል ዓይነቶችን መውሰድ ይችላል። እንዲሁም አነስተኛ መጠን ያለው የበቆሎ እና ገብስ ሊወሰዱ ይችላሉ።
7. አትክልት- ዝቅተኛ ፖታስየም ያላቸው አትክልትን በብዛት ሊወሰዱ ይችላሉ። ነገር ግን ከፍተኛ ፖታስየም ያላቸው አትክልቶች ከመብላቱ በፊት ፖታስየምን ማስወገድ አለባቸው። ጣዕምን ለማሻሻል የሎሚ ጭማቂ መጨመር ይቻላል።
8. ፍራፍሬዎች- እንደ ፖም ፣ ፓፓያ፣ መንደሪን እና ቤሪ የመሳሰሉት አነስተኛ የፖታስየም ይዘት ያላቸው ፍራፍሬዎች በቀን አንድ ጊዜ ብቻ መውሰድ ይቻላል። በኩላሊት እጥበት ቀን ህመምተኞች ማንኛውንም መመገብ ይችላሉ። የፍራፍሬ ጭማቂ እና የኮኮናት ውሃን ግን መወሰድ የለበትም።
9. ወተት እና የወተት ተዋጽኦዎች- እንደ ወተት ያሉ የወተት እና የወተት ተዋጽኦዎች ፣እርጎ እና አይብ ከፍተኛ መጠን ያለው ፎስፈረስ ስለሚይዙ አመጋገብ ላይ መጠናቸው መወሰን አለባቸው። ሌሎች አነስተኛ መጠን ፎስፈረስ ያላቸው የወተት ተዋጽኦዎች እንደ ቅቤ ፣ክሬምአይብ፣ ሪኮታ አይብ፣ ሸርቤትስ፣ ወተት የሌለበት የሰላጣ ማጣፍጫ እና የመሳሰሉትን እንደምትክ መጠቀም ይቻላል።
10. ቀዝቃዛ መጠጦች- ጥቁር ቀለም ያላቸውን ሶዳዎች የፎስፈረስ ይዘት ከፍ ያለ በመሆኑ ከመጠቀም ይከልከሉ። የፍራፍሬ ጭማቂ ወይም የኮኮናት ውሃ ከፍተኛ የፖታስየም ይዘት ሊኖረው ስለሚችል አይወስዱ።
11. ደረቅ ፍራፍሬዎች- ደረቅ ፍራፍሬዎች ፣ ለውዝ፣ዘቢብ፣ቴምር፣ የሰሊጥ ፍሬዎች ፣ ትኩስ ወይም ደረቅ ኮኮናት እንዲወስዱዋቸው አይመከርም።