Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

25. ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም አመጋገብ

የኩላሊት ዋና ተግባር ከሰውነት ውስጥ አላስፈላጊ ግብዐቶችን በማስወገድ ደምን ማጣራት ነው። ኩላሊት ከዚህ በተጨማሪም አላስፈላጊ ውሃን ፣ ማዕድናት እና ውህዶች/ ኬሚካሎች ከሰውነት በማስወገድ እንዲሁም እንደ ሶድየም ፣ ፖታሲየም ፣ ካልሲየም ፣ ፎስፈረስ እና ባይካርቦኔት ያሉ ማዕድናትን በመቆጣጠር ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

ሥር በሰደደ የኩላሊት ህመም የሚሰቃዩ ሕመምተኞች በሰውነት ውስጥ ያሉ ፈሳሾች እና ማእድናትን በመቆጣጠር ላይ ከፍተኛ እክል ሊገጥም ይችላል። በዚህ ምክንያት አግባብ ያለው የውሃ(ፈሳሽ) አወሳሰድ እንዲሁም መደበኛ የገበታ ጨው ወይም ፖታስየም መውሰድ እንኳን በሰውነት የፈሳሽ እና ማእድናትን ሚዛን ላይ መዛባት ሊያስከትል ይችላል።

ጉዳት በደረሰበት ኩላሊት ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ እና የፈሳሽ እንዲሁም የማእድናትን ሚዛን መዛባትን ለመቆጣጠር ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመምተኞች የአመጋገብ ስርአት የህክምና ባለሞያ ባሰፈረላቸው መመሪያ መሰረት ማሻሻል ይኖርባቸዋል። ሥር ለሰደደ የኩላሊት ታካሚዎች ምንም ዓይነት ቋሚ የምግብ መመሪያ የለም ፤ እያንዳንዱ ሕመምተኛ ባለበት የጤና ሁኔታ ፣ እንዲሁም ባለበት የኩላሊት የጉዳት ደረጃ ላይ በመመርኮዝ የተለያየ የአመጋገብ ምክር ይሰጣል።

የአመጋገብ ስርአት ግቦች

  1. የኩላሊት ህመም መባባስ ለመቀነስ እና ደም ማጣራት ህክምናን ማዘግየት
  2. በደም ውስጥ ከመጠን በላይ በሆነ ዩሪያ ምከንያት የሚከሰቱትን መርዛማ ተጽዕኖችን መቀነስ
  3. የተመጣጠነ አመጋገብ በመከተል ከስብ ውጪ የሆነው የሰውነት ክብደት እዳይቀንስ ለመከላከል
  4. የፈሳሽ እና የማዕድናትን መዛባት መቀነስ
  5. የልብና የደም ቧንቧ ህመም ተጋላጭነትን መቀነስ

አጠቃላይ የአመጋገብ ሕክምና መርሆዎች

  • የኩላሊት ደም ማጣራት ህክምና ላልጀመሩ ታካሚዎች የሚወስዱትን የገንቢ ምግብ መጠን በቀን ወደ (<0.8 ግራም /ኪግ የየሰውነት ክብደት/ በቀን) ይገድቡ። የኩላሊት ደም ማጣራት ህክምና ላይ ላሉ ታካሚዎች በህክምናው ወቅት ሊያጡት የሚችልን የገንቢ ምግብ ንጥረ ነገር ለመ ተካት የገንቢ ምግብ መጠንን በቀን (1.0 -1.2 ግራም / ኪግ የሰውነት ክብደት/በቀን) ያስፈልጋል፣
  • በቂ ሃይል ሰጪ ምግብ መውሰድ ሰውነት የሚያስፈልገውን ሃይል እንዲያ ግኝ ይረዳዋል መጠነኛ ቅባት ይጠቀሙ የቅቤን ዘይት እና ቅባት ያላቸው ምግቦችን ከመውሰድ ይታቀቡ፣
  • የሰውንት እብጠት በሚከሰትበት ወቅት የሚወስዱትን የፈሳሽ እና የውሃ መጠን ይገድቡ
  • በምግብዎ ውስጥ ያለውን የሶዲየም የፖታስየም እና ፎስፈረስ መጠን ይገድቡ፣
  • ቫይታሚኖችን እና ጥቃቅን ንጥረ ነገሮችን (ማዕድናትን) በበቂ መጠን መውሰድ። ከፍተኛ አሰር ያላቸውን ምግቦች መመገብ ይመከራል፣

ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመምተኞች የአመጋገብ ዝርዝር እና አመራረጥ ከነማሻሻያው የሚከተለውን ይመስላል:

1. ከፍተኛ የሃይል መጠን ያላቸውን ምግቦች መውሰድ

ሰውነታችን ለዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች፣ የሙቀት መጠንን እንዲሁም እድገት እና የሰውነት ክብደትን ለመጠበቅ በቂ የሆነ ካሎሪ ይፈልጋል። በዋነኝነት ሃይል የሚገኘው ከሃይል ሰጪ ምግቦች እና ከቅባቶች ነው።

ሥር የሰደደ ኩላሊት ህመምተኞች መደበኛ የሃይል ፍላጎት በቀን ከ 35-40 ኪሎ.ካሎሪ/ .. ሲሆን ይህ በቂ ሳይሆን ሲገኝ ሰውነታችን ሃይል ለማቅረብ ገንቢ ምግብን (ፕሮቲንን) ይጠቀማል። ይህ ከፍ ያለ ፕሮቲንን (ገንቢ ምግብን ለሃይል) መጠቀም እንደ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና ከፍተኛ ጎጂ የሆኑ የቆሻሻ ምርቶችን ያስከትላል። ስለሆነም ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመምተኞች በቂ የሃይል መጠን ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው። እንደ ታካሚው ወቅታዊ ክብደት ሳይሆን የበሽተኛውን ተስማሚ ክብደት በመጠቀም የካሎሪ ፍላጎቱን ማስላት አስፈላጊ ነው።

ሃይል ሰጪ ምግቦች /ካርቦሃይድሬት

  • ሃይል ሰጪ ምግቦች /ካርቦሃይድሬት ለሰውነት ዋናው የሃይል ምንጭ ነው። እነሱም ከስንዴ ጥራጥሬ ሩዝ ድንች ፍራፍሬዎች ስኳር ማር ኩኪሶች ኬኮች ጣፋጮች እና ከመጠጦች ውስጥ ይገኛሉ።
  • የስኳር ህመምተኞች እና ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው ታካሚዎች ሃይል ሰጪ ምግቦችን መጠን መገደብ ያስፈልጋቸዋል።
  • የስንዴ ዱቄት እና ሩዝን መመገብ ከፍተኛ የሆነ ሃይል እና አሰር ለማግኘት ይረዳል። ይህም ከብዙ ሃይል ሰጪ ምግቦች የሚገኝ ነው።
  • ሌሎች ቀላል ስኳር አዘል ንጥረ ነገሮች ከጠቅላላው ሃይል ሰጪ ምግቦች መጠን ውስጥ በተለይም የስኳር ህመምተኞች ላይ ከ 20% ያልበለጠ መሆን አለበት።
  • የስኳር ህመምተኛ ያልሆኑ ታካሚዎች ከጉልብት ሰጪ ምግቦች ውስጥ የሚገኙ ሃይል ሰጪ ምግቦች ውስጥ በሚገኙ ሊተኩ ይችላሉ።
  • እነዚህም ከፍራፍሬዎች ፣ ኬኮች ፣ ኩኪሶች ፣ማር እንዲሁም ጣፋጭነታ ቸው የተወሰነ የሆኑ በቸኮሌት ለውዝ ወይም ሙዝ ናቸው።

ቅባት/ስብ

  • ቅባት ለሰውነት አስፈላጊ የሃይል ምንጭ ሲሆን ከሃይል ሰጪ ወይም ከገንቢ ሁለት እጥፍ የበለጠ የሆነ የሃይል ይዘት አለው። እንደ የወይራ ዘይት ፣ የኦቾሎኒ ዘይት ፣ የካኖላ ዘይት ፣ የሱፍ ዘይት እና ለውዝ ያሉት የማይረጉ እና ጥሩስቦች የምንላቸው ሲሆኑ ስጋ ፣ ቅባቱ ያልወጣለት ወተት ፣ ቅቤ ፣ ፎርማጆ ፣ የዘንባባ ገውዝ ፣የአሳማ ጮማ የሚረጉ ወይም ጎጂ ስብ እንላቸዋለን።
  • ሥር የሰደደ ኩላሊት ታካሚዎች ስብ እና ኮሌስትሮል የልብ ህመም ስለሚ ያስከትሉ የቅባት መጠን ላይ ትኩረት መስጠት እና መቀነስ አስፈላጊ ነው።
  • ለጤና ጠቃሚ ከሆኑ ስቦች መካከል የሞኖአንሳቹሬትድ እና የፖሊይአን ሳቹሬትድ ያላቸው የመጠን ድርሻ ላይ ትኩረት መስጠቱ አስፈላጊ ነው። ከመጠን በላይ የሆነ የኦሜጋ -6 [polyunsaturated fatty acids (PUFA)] እንዲሁም ከፍተኛ ኦሜጋ -6 / ኦሜጋ -3 ጥምርታ ጎጂ ሲሆን የዝቅተኛ ኦሜጋ -6 / ኦሜጋ -3ጥምርታ ጠቃሚ ውጤቶችን ያስገኛል። ከነጠላ ዘይት ይልቅ የአትክልት ዘይት ድብልቅ መጠቀም ይህንን ዓላማ ያሳካል። ይህን አይነት ያሉ ንጥረ ነገሮችን የያዙ እንደ ድንች ጥብስ ፣ ዶናት ፣ ለንግድ የተ ዘጋጁ ኩኪዎች እና ኬኮች አደገኛ ሊሆኑ ስለሚችሉ መወገድ አለባቸው።

2. የገንቢ /ፕሮቲን አወሳሰድ መቆጠብ

  • የሰውነት ሕብረ ሕዋሳትን ለመጠገን እና ለመጠበቅ ገንቢ ምግብ/ ፕሮቲን አስፈላጊ ነው። ይኀው ገንቢ ምግብ ቁስሎችን ለመፈወስ እና ከህመም ጋር ለመዋጋት ይረዳል። በኩላሊት የደም ማጣራት ህክምና (ዳያሊሲስ) ላይ ያልሆኑ ታካሚዎች የገንቢ/ ፕሮቲን መጠንን በ (<0.8 ግራም / ኪግ የሰው ነት ክብደት / ቀን) መገደብ የኩላሊት ጫናን መቀነስ እንዲሁም የደም ማጣራት ህክምና /ዳያሊሲስ አስፈላጊነት ጊዜን ለመቀነስ በተጨማሪም የኩላሊት ንቅለ -ተከላ ፍላጎትን ያዘገያል።
  • ከፍተኛ የገንቢ ምግብ /ፕሮቲንን መገደብን ግን ማስውገድ አስፈላጊ ነው ይህም የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ጥንቃቄ መደረግ አለበት።
  • ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመምተኞች ላይ የምግብ ፍላጎት አንስተኛ ወይመ ዝቅተኛ ምሆኑ የተለመደ ነው። ዝቅተኛ የምግብ ፍላጎት እና ጥብቅ የገንቢ ምግብ ክልከላ በአንድነት ተደምረው በምግብ የተጎዱ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ፣ ክብደት መቀነስ ፣ ኃይል ማጣት እና የሰውነት በሽታ የመቋ ቋም አቅም ማነስ ሲያስከትል ይህም የሞት አደጋን ይጨምራል።
  • በተፈጥሮአዊ የገንቢ/ ፕሮቲን ይዘት የበለጸጉ እንደ ሥጋ ፣ ዶሮ ፣ ዓሳ ፣ እንቁላል እና የአኩሪ አተር አይብ ተመራጭ ናቸው። ሥር በሰደደ የኩላ ሊት ህመምተኞች ከፍተኛ የገንቢ/ ፕሮቲን አመጋገቦች (ለምሳሌ አትኪ ንስ) ከመውሰድ መቆጠብ አለባቸው።
  • በተመመሳሳይ ለጡንቻ ማበልጸጊያ ጥቅም ላይ የሚውሉ ተጨማሪዎች እንዲሁም እንደ ክሪያቲኒን ያሉ መድኃኒቶች በሀኪም ተማክሮ ካልሆነ በስ ተቀር መውሰድ አይኖርባቸውም። ሆኖም አንድ ህመምተኛ የኩላሊት ደም ማጣራት ህክምና (ዳያሊሲስ) ላይ ከገባ በኋላ በቀን በሂደቱ ወቅት ሊጠፋ የሚችልን የገንቢ/ፕሮቲን ለመተካት ከ 1.0-1.2 ግራም / ኪግ / በቅን /በሰውነት ክብደት መውሰድ ይኖርበታል።

3. የፈሳሽ አወሳሰድ

ሥር በሰደደ የኩላሊት ህመምተኞች የፈሳሽ አወሳሰድን በተመለከተ ምን ጥንቃቄ መውሰድ አለባቸው?

ኩላሊቶች በሰውነት ውስጥ ከመጠን በላይ ፈሳሽ እንደ ሽንት በማስወገድ ትክክለኛውን የውሃ መጠን በመጠበቅ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። በ ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመምተኞች ላይ የኩላሊት ሥራ እየተዳከመ ይሄዳል ፣ ብዙውን ጊዜ የሽንት መጠኑም ይቀንሳል። መጠኑ የቀነሰ የሽንት መጠን በሰውነት ውስጥ ፈሳሽ እንዲከማች ያደርጋል ፤ ይህም የፊት እብጠት ፣ የእግሮች እና የእጆች እብጠት እና የደም ግፊት ያስከትላል። በሳንባዎች ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት (ፐልሞናሪ ኢዴማ ተብሎ የሚጠራ ሁኔታ) እብጠት እና መጨናነቅ በመፍጠር የትንፋሽ እጥረት እና የመተንፈስ ችግር ያስከትላል። ይህ ካልተቆጣጠሩት ለሕይወት አስጊ ሊሆን ይችላል።

በሰውነት ውስጥ ከመጠን በላይ ውሃ መኖርን የሚጠቁሙ ፍንጮች ምንድን ናቸው?

በሰውነት ውስጥ ከመጠን በላይ ፈሳሽ መኖር ይባላል። የእግር እብጠት ፣ በሆድ ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት ፣ የትንፋሽ ማጠር እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ክብደት መጨመር በሰውነት ውስጥ ከመጠን ያለፈ ፈሳሽ መኖሩን የሚጠቁሙ ፍንጮች ናቸው።

የኩላሊት ህመምተኞች የፈሳሽ አወሳሰድን ለመቆጣጠር ምን ዓይነት ጥንቃቄ መውሰድ አለባቸው?

ፈሳሽ ከመጠን በላይ መጠራቀም ወይም ጉድለትን ለማስወገድ የፈሳሽ መጠን መመዝገብ እና በዶክተሩ ምክር መሠረት ክትትል መደረግ አለበት።

ለእያንዳንዱ የኩላሊት ህመምተኛ የሚፈቀደው ፈሳሽ መጠን የእያንዳንዱ ህመምተኛ የሽንት መጠን እና የሰውነት የፈሳሽ ሁኔታ ላይ መሰረት ያደረገ ስለሚሆን ለእያንዳንዱ የሚመከረው የፈሳሽ መጠን ሊለያይ ይችላል።

ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመምተኛ ምን ያህል ፈሳሽ እንዲወስድ ይመከራል?

  • እብጠት ለሌለባቸው እና በቂ የሽንት ፈሳሽ ላላቸው ታካሚዎች ያልተገ ደበ ውሃ እና ፈሳሽ መውሰድ ይፈቀዳል። የኩላሊት ህመም ያለባቸው ታካ ሚዎች ኩላሊቱን ለመከላከል ብዙ ፈሳሽ መውሰድ አለባቸው የሚል የተ ሳሳተ አመለካከት የተለመደ ነው። የሚፈቀደው ፈሳሽ መጠን በታካሚው የጤና አቋም ሁኔታ እና በኩላሊት ተግባር ላይ መሰረት ያደረገ ነው።
  • እብጠትና የሽንት ፈሳሽ መቀነስ ያጋጠማቸው ታካሚዎች የሚወስዱትን የፈሳሽ መጠን እንዲገደቡ ይደረጋል። እብጠትን ለመቀነስ 24 ሰዓታት ውስጥ የሚወሰደው የፈሳሽ መጠን በየቀኑ ከሚመረተው የሽንት መጠን ያነሰ መሆን አለበት።
  • እብጠት የሌላቸው ህመምተኞች ከመጠን በላይ ፈሳሽ እንዳይኖር እንዲ ሁም የፈሳሽ እጥረት እንዳይከሰት የሚወስዱት የፈሳሽ መጠን በቀን የቀደ መውን ቀን የሽንት መጠን ላይ 500 ሚሊ ሊትር በመደመር ይሆናል። ተጨ ማሪው 500 ሚሊ ሊትር ፈሳሽ በግምት በላብ እና በመተንፈስ ለሚታጡ ፈሳሾች መተኪያ ይሆናል።

ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመምተኞች የዕለት ተዕለት ክብደታቸውን መመዝገብ ለምን ይጠበቅባቸዋል?

  • ታካሚዎች ፈሳሽን ለመቆጣጠርና በሰውነት ውስጥ ያለው ፈሳሽ መጠን መጨመር ወይም ማነስን ለመለየት የእለት ተእለት ክብደታቸውን መዝግቦ መያዝ አለባቸው። የፈሳሽ አወሳሰድን በተሰጠው መመሪያ መሰረት በጥብቅ በሚከተሉበት ጊዜ የሰውነት ክብደት አይለዋወጥም። በህመምተኞቹ ላይ ድንገተኛ የክብደት መጨመር ከመጠን በላይ ፈሳሽ ከመውሰድ የተነሳ የሚመጣ ከፍ ያለ የሰውነት ፈሳሽ መጠን መኖሩን ያሳያል። ክብደት መጨመር ለህመምተኛው የፈሳሽ አወሳሰድ መገደብ ላይ ተጨማሪ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ያመለክታል። ክብደት መቀነስ ብዙውን ጊዜ በፈሳሽ መገደብ እንዲሁም በዳዩሪቲክስ/ በሚያሸኑ መድሃ ኒቶች ውጤት ምክንያት ይከሰታል።

ፈሳሽ አወሳሰድን ለመቀነስ ጠቃሚ ምክሮች

ፈሳሽ አወሳሰድን መገደብ ከባድ ነው ነገር ግን እነዚህ ምክሮች ይረዱዎታል-

  1. በየቀኑ በተመሳሳይ ጊዜ እራስዎን ይመዝኑ እና በዚህ መሠረት ፈሳሽ አወሳሰድን ያስተካክሉ።
  2. ሐኪሙ በአንድ ቀን ውስጥ ምን ያህል ፈሳሽ መጠቀም እንደሚፈቀድ ምክር ይሰጥዎታል። በዚህ መሠረት ያስሉ እና የተለካውን የፈሳሽ መጠን በየቀኑ ይውሰዱ። ፈሳሽ መውሰድ ውሃ ብቻ እንዳልሆነ ያስታውሱ እንደ ሻይ ፣ ቡና ፣ ወተት ፣ ጭማቂ ፣ አይስክሬም ፣ ቀዝቃዛ መጠጦች ፣ ሾርባ እና ከፍተኛ የውሃ ይዘት ያላቸው ሌሎች ምግቦች እንደ ሐብሐብ ወይን ፣ሰላጣ ቲማቲም ሴሊየሪ መረቅ፣ ጄላቲን እና የቀዘቀዙ ምግቦችን ያካትታል።
  3. ጨዋማ ቅመም የበዛባቸው እና የተጠበሱ ምግቦች ጥማትን በመጨመር ከፍተኛ ፈሳሽ ስለሚያስወስዱ እነዚን ምግቦች መውሰድ ይቀንሱ።
  4. ሲጠማዎ ብቻ ይጠጡ። እንደ ልማድ አይጠጡ ወይም ሁሉም እየጠጣ ሰለሆነ አይጠጡ።
  5. በሚጠሙበት ጊዜ ትንሽ ውሃ ብቻ ወይም በረዶ ይውሰዱ። አንድ ትንሽ በረዶ ይውሰዱና ይምጠጡት። በረዶ በአፍ ውስጥ ረዘም ላለ ጊዜ ስለሚቆይ ከተመሳሳይ የዉሃ መጠን ይልቅ የበለጠ ጥምን አርኪ ነው። በረዶ እንደተወሰደ ፈሳሽ መቁጠርዎን አይርሱ። ለስሌት እንዲመች መጠኑ የታወቀ ውሃ ያቀዝቅዙ።
  6. የአፍ ድርቀትን ለማስቀረት ውኃውን ሳይውጡ መጉመጥመጥ ይችላል። የአፍ ድርቀትን ማስቲካ በማኘክ ጠንካራ ከረሜላ በመምጠጥ ፣ የሎሚ ሽብልቅ ወይም ሜንትስ እን አፍን ለማራስ አፍ መታጠብያን በመጠቀም መቀንስ ይችላል።
  7. መጠጥዎን ለመገደብ ሁል ጊዜ አነስተኛ መጠን ያለው ኩባያ እና ብርጭቆ ይጠቀሙ።
  8. መድሃኒት በሚወስዱበት ጊዜ ምግብ ከተመገቡ በኋላ ይውሰዱ። ለመድኃኒት መውሰጃ ተጨማሪ የውሃ ፍጆታን ለመቀነስ ይረዳል።
  9. አንድ ታካሚ ራሱን በስራ መጥመድ አለበት። ራሱን በስራ ያልጠመደ ሕመምተኛ ብዙ ጊዜ ውሃ የመጠጣት ፍላጎት ይሰማዋል።
  10. በስኳር ህመምተኞች ውስጥ ያለው ከፍተኛ የስኳር መጠን ጥማትን ሊያሳድግ ይችላል። ጥምን ለመቀነስ የደም ስኳር መጠንን መቆጣጠር በጣም አስፈላጊ ነው። ሞቃታማ የአየር ጠባይ የአንድ ሰው ጥማት ስለሚጨምር በቀዝቃዛ ቦታ መኖር ተመራጭ እና የሚመከር ነው።

የታዘዘውን የፈሳሽ መጠን እንዴት በየቀኑ ይለካል እና ይወስዳል?

  • በሐኪሙ የታዘዘውን ትክክለኛ የፈሳሽ መጠን ጋር እኩል በሆነ ማጠራቀ ሚያ ውሀ ይሙሉ።
  • ህመምተኛው ለቀን እንዲወሰድ ከተፈቀደው የፈሳሽ መጠን ውጪ መውሰድ እንደማይፈቀድ ማወቅ አለበት።
  • ህመምተኛው የተወሰነ መጠን ያለው ፈሳሽ በወሰደ ቁጥር ተመሳሳይ የውሃ መጠን ከውኃ ማጠራቀሚያ ውስጥ መወገድ አለበት።
  • እቃው ውስጥ ተጨማሪ ውሃ በማይኖርበት ጊዜ ህመምተኛው የዕለቱ የፈሳሽ ኮታ በመጠናቀቁ ከዚያ በኋላ ተጨማሪ መጠጣት የለበትም።
  • ተጨማሪ የፈሳሽ ፍላጎትን ለማስወገድ አጠቃላይ የፈሳሽ መጠንን በቀን ውስጥ በእኩል ማሰራጨት ይመከራል።
  • ይህ ዘዴ በየቀኑ በመደጋገም ከተከታተሉ ውጤቱን ያሳያል፤ ተገቢውን ፈሳሽ መጠን ለመውሰድ እንዲሁም ከመጠን በላይ ፈሳሽ መውሰድን ይከላከላል።

4. በምግብ ውስጥ ጨው (ሶዲየም) መገደብ ዝቅተኛ ሶዲየም ያለው ምግብ ሥር በሰደደ የኩላሊት ህመም ህመምተኞች ለምን ይመከራል?

  • በአመጋገባችን ውስጥ የሶዲየም መኖር የሰውነት የደም መጠን እና የደም ግፊትን ለመቆጣጠር አስፈላጊ ነው።
  • ኩላሊታችን የሶዲየም መጠንን ለመቆጣጠር ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
  • ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ባላቸው ታካሚዎች ውስጥ ኩላሊቶቹ አላስፈላጊ ሶድየምና ፈሳሾችን ማስወገድ ስለማይችሉ ከመጠን በላይ ሶዲየም እና ፈሳሽ በሰውነት ውስጥ መጠራቀም ይጀምራል።
  • በሰውነት ውስጥ ያለው የሶዲየም መጠን መጨመር ወደ መጠማት ፣ እብጠት መኖር፣ የትንፋሽ እጥረት እና የደም ግፊት መጨመር ያስከት ላል። እነዚህን ችግሮች ለመከላከል ወይም ለመቀነስ የኩላሊት ህመም ተኞች በምግባቸው ውስጥ የሶዲየም/የጨው መጠንን መገደብ አለባ ቸው።

በሶዲየም እና በጨው መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

  • ሶድየም እና ጨው የሚሉት ቃላት በተለምዶ በተመሳሳይ ቃላትነት ያገለግ ላሉ። ጨው (የጠረጴዛ ጨው) ሶዲየም ክሎራይድ ሲሆን 40% ሶዲየም ይይዛል። በአመጋገባችን ውስጥ የሶዲየም መሠረታዊ ምንጭ ጨው ነው። ይሁን እንጂ ጨው ብቸኛው የሶዲየም ምንጭ ግን አይደለም። በም ግባችን ውስጥ ሌሎች ጥቂት የሶዲየም ውህዶች አሉ እንደ-
  • የሶዲየም አልጃይኔት፡ በአይስ-ክሬም እና በቸኮሌት ወተት ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል
  • ሶድየም ባይካርቦኔት፡ እንደ መጋገሪያ ዱቄት እና ሶዳ ጥቅም ላይ ይውላል
  • ሶዲየም ቤንዞኤት፡ በሶስ ውስጥ እንደ ማቆያ ጥቅም ላይ ይውላል
  • የሶዲየም ሲትሬት፡ ለጀልቲን ለጣፋጮች እና መጠጦች ጣዕም
  • ሶድየም ናይትሬት፡ የተሰራ ስጋን ለማቆየት እና ለማቅለም ያገለግላል
  • ሶዲየም ሳክሃራይድ፡ እንደ ሰው ሰራሽ ማጣፈጫ ያገለግላል
  • ሶዲየም ሰልፋይት፡ የደረቁ ፍራፍሬዎች እንዳይበከሉ ለመከላከል ይጠቅ ማል ከላይ የተጠቀሱት ውህዶች ሶዲየም ይይዛሉ ግን በጣዕም ጨዋማ አይደሉም። በእነዚህ ውህዶች ውስጥ ሶዲየም ተደብቋል።

አንድ ሰው ምን ያህል ጨው መውሰድ አለበት?

  • የተለመደው የጨው መጠን በቀን ከ 2.3 እስከ 1.5 ግራም ነው። ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ ያላቸው ታካሚዎች ጨው በዶክተሩ አስተያየት መሠረት መውሰድ አለባቸው። የኩላሊት በሽታ ህመምተኞች እብጠት እና ከፍተኛ የደም ግፊት ካለባቸው ብዙውን ጊዜ በቀን ከ 1 ግራም በታች ጨው/ እንዲወስዱ ማለትም ከ1 የሻይ ማንኪያ ያነሰ ጨው በ24 ሰአት ውስጥ (< 2 ግራም ሶድየም) እንዲወስዱ ይመከራሉ።

የትኞቹ ምግቦች ከፍተኛ መጠን ያለው ሶዲየም ይይዛሉ?

በሶዲየም የበለጸጉ ምግቦች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ

  1. የጠረጴዛ ጨው (የምግብ ጨው) የመጋገሪያ ዱቄት
  2. እንደ የታሸጉ ምግቦች ፈጣን ምግቦች እና ደሊ ስጋዎች ያሉ የተቀነባበሩ ምግቦች
  3. ተዘጋጅተው የሚሸጡ ወጦች
  4. ቅመማ ቅመሞች የሶያ ሶስ አኩሪ አተር እና ክኖር
  5. ብስኩት ኬኮች ፒዛ እና ዳቦን ያሉ የተጋገሩ የምግብ አይነቶች
  6. ዋፈርስ፣ ቺፕስ ፈንዲሻ ጨዋማ ለውዝ ጨዋማ ደረቅ ፍራፍሬዎች እንደ የካሽ ፍሬ እና ፒስታኪዮስ
  7. የንግድ ጨዋማ ቅቤ እና የገበያ አይብ /ፎርማጆ
  8. እንደ ኑድል ስፓጌቲ ማካሮኒ እና ፈጣን ምግቦች
  9. አትክልቶች እንደ ጎመን አበባ ጎመን ስፒናች ራዲሽ ቢትሮት እና የበቆሎ ቅጠል
  10. የኮኮናት ውሃ
  11. እንደ ሶዲየም ባይካርቦኔት ክኒኖች፣ ፀረ-አሲዶች የላክሳቲቭ መድኃኒቶች
  12. ከእንሰሳት ተዋጻኦ የሆኑ እንደ ሥጋ ከዶሮ እና የእንስሳት ኩላሊት፣ ጉበት እና አንጎል
  13. እንደ ሸርጣን ሎብስተር ኦይስተር ሽሪምፕ ዘይት ዓሳ ያሉ የባህር ምግቦች

ሶዲየም በምግብ ውስጥ ለመቀነስ ተግባራዊ ምክሮች

  1. የጨው መጠን መገደብ እና በአመጋገብ ውስጥ ተጨማሪ ጨው እና ቤኪንግ ሶዳ ማስወገድ። ምግብ ያለ ጨው ያብስሉ እና የተፈቀደውን ያክል ብቻ ጨው በተናጠል ይጨምሩ። ይህ የጨው አጠቃቀምን ለመቀነስ እና በዕለት ተዕለት ምግብ ውስጥ የታዘዘውን የጨው መጠን መጠቀም ለማረጋገጥ የተሻለው አማራጭ ነው።
  2. ከፍተኛ የሶዲየም ይዘት ያላቸውን ምግቦች ያስወግዱ (ከላይ እንደተጠቀሰው)
  3. ጨው እና ጨዋማ ቅመሞችን በጠረጴዛ ላይ ወይም በአጠቃላይ አያቅርቡ። ከመመገቢያ ጠረጴዛው ላይ የጨው ማቅረቢያውን ያስወግዱ።
  4. የታሸጉ ምግቦች መሸፈኛዎች ለጨው ብቻ ሳይሆን ለሌላው ሶድየም ውህዶችን ይዘት ይፈልጉ። የታሸጉ ምግቦችን በጥንቃቄ ያንብቡ ፣ ይፈትሹ እና ይምረጡ። ሶዲየም-ነፃወይም ዝቅተኛሶዲየምየምግብ ምርቶች መሆኑን እና በእነዚህ ምግቦች ውስጥ ሶዲየም ለመተካት ፖታስየም ጥቅም ላይ አለመዋሉን እርግጠኛ ይሁኑ።
  5. የመድኃኒቶችን የሶዲየም ይዘት ይፈትሹ።
  6. ከፍተኛ የሶዲየም ይዘት ያላቸውን አትክልቶች ቀቅለው ውሃውን ይድፉት። ይህ በአትክልቶች ውስጥ ፖታሲየም ይዘትን ሊቀንስ ይችላል።
  7. ዝቅተኛ የጨው አመጋገብን ጣፋጭ ለማድረግ ሌሎች ቅመሞችን መጨመር ይቻላል። እንደ ነጭ ሽንኩርት ፣ ሽንኩርት ፣ የሎሚ ጭማቂ ፣ የስጎ ቅጠል ታማርን ዱባ ሆምጣጤ ቀረፋ ቅርንፉድ ነትመግ ጥቁር አዝሙድ ያሉትን መጠቀም።
  8. ጥንቃቄ! የጨው መተኪያዎች ከፍተኛ የፖታሲየም ይዘት ስለሚኖራቸው ከመጠቀም ይቆጠቡ። የጨው መተኪያዎች ውስጥ የሚገኝ ከፍተኛ የፖታስየም ይዘት በኩላሊት ታማሚዎች ውስጥ በደም ውስጥ ያለውን የፖታስየም መጠን ወደ አደገኛ ደረጃዎች ሊያባብስ ይችላል።
  9. የለሰለሰ ውሃ (የተጣራ) ውሃ አይጠቀሙ። በውሃ ማለስለስ ሂደት ውስጥ ካልሲየም በሶዲየም ይተካል በተገላቢጦሽ በኦስሞሲስ የተጣራ ውሃ ሶዲየምን ጨምሮ በሁሉም ማዕድናት ይዘት አነስተኛ ነው።
  10. በምግብ ቤቶች ውስጥ ምግብ በሚመገቡበት ጊዜ አነስተኛ ሶዲየም የያዙ ምግቦችን ይምረጡ።

5. በአመጋገብ ውስጥ የፖታስየም መገደብ

የኩላሊት ህመምተኞች በአመጋገብ ውስጥ ፖታስየም እንዲገድቡ ለምን ይመከራሉ?

የጡንቻዎች የነርቮች ትክክለኛ አሠራር እና የልብ ምት በመደበኛነት እንዲመታ ማድረግ የፖታስየም ማዕድን በሰውነት ውስጥ አስፈላጊ ተግባራቶች ናቸው። በሰውነት ውስጥ ያለው የፖታስየም መጠን ሚዛናዊነት ፖታስየም የያዙ ምግቦችን በመመገብ እና ከመጠን በላይ የፖታስየምን በሽንት ውስጥ በማስወገድ ይጠበቃል። ሥር በሰደደ የኩላሊት በሽታ ህመምተኞች ፖታሲየምን ከሽንት ውስጥ ማስወገድ ደካማ ስለሆነ በደም ውስጥ ያለው ፖታስየም በከፍተኛ መጠን ሊጠራቀም ይችላል። ይህ ሁኔታ ሃይፐርካሌሚያ ተብሎ ይጠራል።

የሃይፐርካሌሚያ መከሰት የፔሪቶኒያል ዲያሊሲስ የሚያደርጉ ሕመምተኞች ከሄሞዲያሊሲስ ላይ ካሉት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ነው። ይህ የሆነው በፔሪቶኒያል ዲያሊሲስ ጊዜ ዲያሊሲሱ ቀጣይነት ያለው ሲሆን በሄሞዲያሊሲስ ጊዜ ግን አልፎ አልፎ ይደረጋል።

ከፍተኛ የፖታስየም መጠን ከፍተኛ የጡንቻ ድክመት ወይም አደገኛ ሊሆን የሚችል ያልተለመደ የልብ ምት ሊያስከትል ይችላል። ፖታስየም በጣም ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ ልብ ባልታሰበ ሁኔታ መምታት ማቆም እና ድንገተኛ ሞት ያስከትላል። ከፍተኛ የፖታስየም መጠን በግልጽ የሚታዩ ክስተቶች ወይም ምልክቶች ሳይኖሩ ለሕይወት አስጊ ሊሆን ይችላል ስለዚህ ዝምተኛ ገዳይ በመባል ይታወቃል። የፖታስየም አስከፊ ጉዳቶችን ለማስወገድ የኩላሊት ህመምተኞች በአመጋገብ ውስጥ ፖታስየም እንዲገደብ ይመከራል።

በደም ውስጥ መደበኛ የፖታስየም መጠን ምንድነው? መቼ ነው ከፍተኛ ተብሎ የሚቆጠረው?

  • መደበኛው የደም ፖታስየም (በደም ውስጥ ያለው የፖታስየም መጠን) 3.5 . / ሊእስከ 5.0 . / ነው።
  • የደም ውስጥ ፖታስየም 5.0 እስከ 6.0 . / ሊ፣ በሚሆንበት ጊዜ የፖታስየም አመጋገብን መወሰን ያስፈልጋል።
  • የደም ውስጥ ፖታስየም ከ 6.0 ./ ሊሲበልጥ፤ ይህን ለመቀነስ ንቁ የህክምና ክትትል ያስፈልጋል።
  • 7.0 . / ሊየሚበልጥ የሴረም ፖታስየም ለሕይወት አስጊ ነው። እንደ የድንገተኛ ጊዜ ዳያሊሲስ ያለ አስቸኳይ ህክምና ይፈልጋል።

በፖታስየም ይዘት መሠረት የምግብ ምድቦች

  • በደም ውስጥ ያለውን ትክክለኛ የፖታስየም መጠንን ለመቆጣጠር የምግብ አወሳሰድ በሐኪሙ ምክር መሠረት መሆን አለበት። በፖታስየም ይዘቶች ላይ በመመርኮዝ ምግቦችን በሦስት የተለያዩ ቡድኖች ይመደባሉ (ከፍተኛ መካከለኛ እና ዝቅተኛ) ፖታስየም አዘል ምግቦችን
  • ከፍተኛ ፖታስየም = 200 ./ 100 ግራም ምግብ መካከለኛ ፖታስ የም = 100 እስከ 200 . / 100 ግራም ምግብ
  • ዝቅተኛ ፖታስየም = 100 . / 100 ግራም ምግብ በታች

ከፍተኛ የፖታስየም ይዘት ያላቸው ምግቦች

  • ፍራፍሬዎች- ትኩስ አፕሪኮት የበሰለ ሙዝ ቺኩ (ሳፖዲላ) ትኩስ ኮኮናት ፣ ካስታርድ አፕል ፣ ጉስቤሪ ፣ ጉአቫ ፣ ኪዊ ፍሬ ፣ የበሰለ ማንጎ ፣ ብርቱካን ፓፓያ ፒች ሮማን እና ፕለም
  • አትክልቶች- ብሮኮሊ ክላስተር ባቄላ እንጉዳይ ጥሬ ፓፓያ ድንች ዱባ ስፒናች ጣፋጭ ድንች እና ቲማቲም
  • ደረቅ ፍሬዎች- አልሞንድ ካሾ ፍሬ ቴምር ደረቅ በለስ ዘቢብ እና ዋልኖት
  • እህሎች: የስንዴ ዱቄት
  • ጥራጥሬዎች፡ ቀይ እና ጥቁር ባቄላ እና ሙን (ሞንጎ) ባቄላ
  • ቬጀቴሪያን ያልሆነ ምግብ፡ እንደ አንቾቪ እና ማኬሬል ያሉ ዓሳዎች፣ ሎብ ስተር እና ሸርጥ አሳ እና የበሬ ሥጋ
  • መጠጦች: የኮኮናት ውሃ ፣ የታመቀ ወተት ፣ የጎሽ ወተት ፣ ላም ወተት ፣ የቸኮሌት መጠጦች ፣ ትኩስ የፍራፍሬ ጭማቂዎች ፣ ሾርባ ፣ ቢራ ፣ ወይን እና ብዙ አየር ያላቸው መጠጦች
  • ልዩ ልዩ- ቸኮሌት ቸኮሌት ኬክ ቸኮሌት ክሬም የሎና ጨው (የጨው ምትክ) ድንች ቺፕስ እና የቲማቲም ሶስ

ምግቦች መካከለኛ የፖታስየም ይዘት

  • ፍራፍሬዎች: የበሰለ ቼሪ ወይን ፒር ጣፋጭ ሎሚ እና ሐባብ
  • አትክልቶች: ቀይ ስር ፣ ጥሬ ሙዝ ፣ መራራ ጎመን ፣ ጎመን ፣ ካሮት ፣ የአበባ ጎመን የፈረንሳይ ባቄላ ኦክራ (ወይዛዝርት ጣት) ጥሬ ማንጎ ሽንኩ ርት ራዲሽ አረንጓዴ አተር ጣፋጭ በቆሎ እና የአበባ ቅጠል
  • እህሎች፡ ገብስ ፣ ፉርኖ ዱቄት ፣ ከስንዴ የተሰራ ኑድል ፣ ዱቄት ፣ የሩዝ ፍሌክስ (የተጨመቀ ሩዝ) እና የስንዴ ቬርሚሴሊ
  • አትክልት ያልሆነ ምግብ ፡ ጉበት
  • መጠጦች እርጎ

ዝቅተኛ የፖታስየም ይዘት ያላቸው ምግቦች

  • ፍራፍሬዎች፡ አፕል ብላክቤሪ ሎሚ አናናስ እና እንጆሪ
  • አትክልቶች፡ ዱባ ሰፊ ባቄላ ጮርቃ ቃርያ፣ ነጭ ሽንኩርት ሰላጣ እና ሹል ጎመን
  • እህሎች፡ ሩዝ የስንዴ ዱቄት
  • ጥራጥሬዎች፡ አረንጓዴ አተር
  • አትክልት ያልሆነ ምግብ፡ የበሬ የበግ የአሳማ ሥጋ ዶሮ ሥጋ እና እን ቁላል
  • መጠጦች፡ ኮካ ኮላ ቡና የሎሚ ጭማቂ እና ሶዳ
  • ልዩ ልዩ፡ የደረቀ ዝንጅብል ማር አዝሙድ ቅጠል ሰናፍጭ ጥቁር ፔፐር እና ኮምጣጤ

ፖታስየም በምግብ ውስጥ ለመቀነስ ተግባራዊ ምክሮች

  1. በቀን ቢያንስ አንድ ፍራፍሬ ይመገቡ በተለይም በአነስተኛ ፖታስየም ይዘት ያለው።
  2. በየቀኑ አንድ ኩባያ ሻይ ወይም ቡና መጠቀም።
  3. ፖታስየም ያላቸው አትክልቶች የፖታስየም መጠኑን ከቀነሱ በኋላ መወሰድ አለባቸው (ከዚህ በታች እንደተጠቀሰው)
  4. የኮኮናት ውሃ የፍራፍሬ ጭማቂዎች እና ከፍተኛ ፖታስየም ይዘቶች ያላቸውን ምግቦች ያስወግዱ (ከላይ እንደተጠቀሰው)
  5. ሁሉም ምግብ ማለት ይቻላል የተወሰነ ፖታስየም ይይዛሉ ስለሆነም ዋናው ቁልፉ ዝቅተኛ የፖታስየም ይዘት ያላቸው ምግቦችን መምረጥ ነው።
  6. የፖታስየም መገደብ ለቅድመ ዲያሊሲስ ህመምተኞች ብቻ ሳይሆን ዲያሊሲስ ከጀመሩ በኋላም ቢሆን አስፈላጊ ነው።

በአትክልቶች ውስጥ የፖታስየም ይዘት እንዴት ይቀነሳል?

  • አትክልቶችን ልጠው ወደ ትናንሽ ቁርጥራጮች መቆራረጥ።
  • አትክልቶችን ሞቅ ባለ ውሃ አጥበው በአንድ ትልቅ ማሰሮ ውስጥ ያስገቡ።
  • ማሰሮውን በሙቅ ውሃ ይሙሉ (የውሃው ብዛት የአትክልቶችን መጠን ከአራት እስከ አምስት እጥፍ መብለጥ አለበት) እና ቢያንስ አትክልቶቹን ለአንድ ሰዓት ያርሷቸው።
  • አትክልቶቹን 2-3 ሰዓታት ካጠቡ በኋላ ሶስት ጊዜ በሞቀ ውሃ ያለቅ ልቋቸው።
  • በመቀጠል አትክልቶቹን በተጨማሪ ውሃ ይቀቅሏቸው። ውሃውን ያስወ ግዱ።
  • የተቀቀለውን አትክልቶች እንደፍላጎትዎ ያብስሏቸው።
  • ምንም እንኳን በአትክልቶች ውስጥ ያለውን የፖታስየም መጠን መቀነስ ቢችሉም ፣ ከፍተኛ ፖታስየም የያዙ አትክልቶችን አለመመገብ ወይም በትንሽ መጠን ብቻ መውሰድ ተመራጭ ነው።
  • ቫይታሚኖች በበሰሉ አትክልቶች ውስጥ የሚጠፉ በመሆናቸው ተጨማሪ የቫይታሚን መተኪያዎች እንደ ሐኪሙ ምክር መውሰድ ይኖርባቸዋል። ፖታስየም ከድንች ለማስወገድ ልዩ ምክሮች።
  • ድንቹን ወደ ትናንሽ ቁርጥራጮች መቁረጥ ወይም መፍጨት አስፈላጊ ነው ፤ በዚህ ላይ የድንች ቁርጥራጮች ውኃ በማድረግ ከድንች የፖታስ የም ብክነትን እንዲጨምር ይረዳል።
  • ድንቹን ለመንከር ወይንም ለማፍላት ያገለገለው የውሃ ሙቀት ልዩነት ያመጣል።
  • ድንቹን ለመንከር ወይንም ለማፍላት ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ መጠቀም ተገቢ ነው።

6. በምግብ ውስጥ ፎስፈረስ መገደብ የኩላሊት ህመም ህመምተኞች ዝቅተኛ ፎስፈረስ አመጋገብን ለምን መከተል አለባቸው?

  • ፎስፈረስ አጥንትን ጠንካራ እና ጤናማ ለማድረግ አስፈላጊ ማዕድን ነው በምግብ ውስጥ ያለው ከመጠን በላይ ፎስፈረስ በሽንት በኩል ከሰው ነት ይወገዳል። ይህ የደምን ፎስፈረስ መጠን ይጠብቃል።
  • በደም ውስጥ ያለው ፎስፈረስ መደበኛ መጠን 4.0 እስከ 5.5 . / . ነው።
  • ሥር በሰደደ የኩላሊት ህመም ያላቸው ታካሚዎች በምግብ የወሰዱትን ተጨማሪ ፎስፈረስ ማስወገድ አይችሉም ፤ስለዚህ ደም ውስጥ ያለው መጠን ከፍ ይላል። ይህ የጨመረው ፎስፈረስ ከአጥንቶች ውስጥ ካልሲ የምን በማውጣት አጥንቶችን ደካማ ያደርጋቸዋል።
  • በሰውነት ውስጥ የፎስፈረስ ደረጃ መጨመር ማሳከክን ፣ የጡንቻዎች እና የአጥንት ድክመቶች የአጥንት ህመሞች የአጥንት ጥንካሬ እና የመገ ጣጠሚያ ህመምን የመሰሉ ብዙ ችግሮችን ያስከትላል። ይህ ለአጥንት ስብራት ተጋላጭነትን ይጨምራል።

የትኞቹን ከፍተኛ ፎስፈረስ የያዙ ምግቦች መቀነስ ወይም መተው አለባቸው?

ከፍተኛ ፎስፈረስ የያዙ ምግቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ

  • ወተት እና የወተት ተዋጽኦዎች፡ አይብ ፣ ቸኮሌት ፣ የታመቀ ወተት ፣ በረዶ እና ክሬም
  • ደረቅ ፍራፍሬዎች፡ የካሽ ፍሬዎች የለውዝ ፣ ፒስታስኪዮስ ደረቅ ኮኮናት ዋልነቶች
  • ቀዝቃዛ መጠጦች፡ ኮላ ቢራ
  • ካሮት በቆሎ ለውዝ አተር ስኳር ድንች
  • የእንስሳት ፕሮቲን: ስጋ ዶሮ አሳ እና እንቁላል

7. ከፍተኛ ቫይታሚን እና ፋይበር መውሰድ

ሥር በሰደደ የኩላሊት ህመም ህመምተኞች በቅድመ-ዲያሊሲስ ወቅት በዝቅተኛ የምግብ ፍላጎት እና የኩላሊት ህመም መባባስን ለማዘግየት ሲባል ከመጠን በላይ የተከለከለ አመጋገብ በአጠቃላይ በቂ ያልሆነ የቪታሚኖች አቅርቦት ይኖራቸዋል። የተወሰኑ ቫይታሚኖች - በተለይም በውሃ ውስጥ የሚሟሙ ቫይታሚኖች እንደ ቫይታሚን ቢ ፣ ቫይታሚን ሲ እና ፎሊክ አሲድ - በዲያሊሲስ ወቅት ይጠፋሉ።

የእነዚህ ቫይታሚኖች አጠር አመጋገብ ወይም የቪታሚኖች መጓደልን ለማካካስ የኩላሊት ህመምተኞች ብዙውን ጊዜ በውሃ ውስጥ የሚሟሟ ቫይታሚኖችን እና ተጨማሪ ጥቃቅን ንጥረነገሮች ያስፈልጓቸዋል። ከፍተኛ የፋይበር መጠን ሥር በሰደደ የኩላሊት በሽታ ህመምተኞች ጠቃሚ ነው። ስለሆነምታካሚዎች በቪታሚን የበለፀጉ ትኩስ አትክልቶችን እና ፍራፍሬዎችን የበለጠ እንዲወስዱ፤ እንዲሁም ከፍተኛ መጠን ያለው የፖታስየም ይዘት ያላቸውን ምግቦች እንዳይወስዱ ይመከራል።

ዕለታዊ ምግብን በእቅድ ስለማዘጋጀት

  • ለኩላሊት ህመምተኞች የየቀኑ የምግብ እና የውሃ መጠን አወሳሰድ በአመጋገብ ባለሙያው እና በኩላሊት ሃኪሙ /በኔፍሮሎጂስቱ ምክር መሠረት ይታቀዳል።

በምግብ እቅድ የተለመዱ መርሆዎች፡

1.    የውሃ እና ፈሳሽ ምግብ አወሳሰድ፡- ፈሳሽ አወሳሰድ በሐኪሙ ምክር መሠረት ውስን መሆን አለበት። ዕለታዊ ክብደት ተጠብቆ መቆየት አለበት። በክብደቱ ውስጥ ማንኛውም ተገቢ ያልሆነ ጭማሬ ከአስፈላጊ ከተስተዋለ ከተገቢዉ በላይ ፈሳሽ መውሰድን ሊያመለክት ይችላል።

2.   ሃይል ሰጪ ምግብ /ካርቦሃይድሬት፡- ሰውነት በቂ ሃይል ማግኘቱን ለማረጋገጥ ኩላሊት በሽታ ህመምተኞች ተያያTh የስኳር ህመምተኛ ካልሆኑ ስኳር ወይም ግሉኮስ የያዘ ምግብ መውሰድ ይችላሉ።

3.   ገንቢ ምግብ / ፕሮቲን፡ ሥጋ ፣ ወተት ፣ እህሎች ፣ ጥራጥሬዎች ፣ እንቁላል እና ዶሮ ዋናዎቹ የገንቢ ምግብ ምንጮች ናቸው። በኩላሊት የደም ማጣራት ህክምና (ዲያሊሲስ) ያልጀመሩ የኩላሊት ህመምተኞች አመጋገብ የገንቢ ምግብ /ፕሮቲንን ወደ <0.8 ግራም / ኪግ አካል ክብደት / ቀን እንዲወስን ይመከራል። በኩላሊት የደም ማጣራት ህክምና (ዲያሊሲስ) የጀመሩ ህሙማን የአመጋገብ ምጣኔን ከ1-1.2 ግራም / ኪግ የሰውነት ክብደት / ቀን ከፍ ማድረግ ይቻላል።

የፔሪቶኒየል የደም ማጣራት ህክምና /ዳያሊስስን የሚያካሂዱ ታካሚዎች በየቀኑ እስከ 1.5 ግራም / ኪግ/በቀን የሰውነት ክብደት ወሳኝ የገንቢ ምግብ ያስፈልጋቸዋል። የእንስሳት ተዋጽ ገንቢ ምግብ ሁሉንም አስፈላጊ አሚኖ አሲዶች ይይዛሉ (ስለሆነም የተሟሉ የገንቢ ምግብ ይባላሉ ወይም ከፍተኛ ባዮሎጂያዊ እሴት ያላቸው ይባላሉ) እንዲሁም ተስማሚ ይሆናሉ ፤ ነገር ግን ከእነዚህ የገንቢ ምግብ /ፕሮቲኖች የደም ማጣራት ህክምና /ዲያሊሲስ ያልጀመሩ ታካሚዎች የሚመገቡትን መጠን መቀነስ አለባቸው ምክንያቱም ለሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም መባባስን እና መፋጠን መክንያት ይሆናል።

4.  ቅባት- ቅባት ጥሩ የካሎሪ ምንጭ እንደመሆናቸው መጠን እንደ ኃይል ምንጭ ሊወሰዱ ይችላሉ። ሞኖአንሳቹሬትድ እና ፖሊአንሳቹሬትድ ቅባቶችን በወይራ ዘይት ፣ በሱፍ አበባ ዘይት ፣ በካኖላ ዘይት ወይም በአኩሪ አተር ዘይት መልክ ውስን በሆነ መጠን ሊወሰዱ ይችላል። በእንስሳት ስብ ውስጥ የሚገኙ የተሟሉ ቅባቶችን ከመጠቀም ይቆጠቡ።

5.    ጨው- አብዛኛዎቹ ህመምተኞች አነስተኛ የጨው ምግብ እንዲመገቡ ይመከራሉ። "ጨው ያልተጨመረበት" አመጋገብን ማክበር ጥሩ ነው። ዝቅተኛ የሶዲየም ምግቦች በውስጣቸው የያዙት የጨው መተኪዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ፖታስየም አለመያዛቸውን ያረጋግጡ። የምግብ ስያሜዎችን እንደ ሶዲየም ባይካርቦኔት ያሉ ሶዲየም ለያዙ ሌሎች ምግቦች ይፈትሹና እንደ(ቤኪንግ ዱቄት) ያሉትን ያስወግዱ።

6.   እህሎች- እንደ ጠፍጣፋ ሩዝ ያሉ ወይም ሌሎች የሩዝ ምርቶች ሊወሰዱ ይችላሉ። የአንድ ዓይነት ጣዕም መሰላቸትን ለማስወገድ አንድ ሰው እንደ ስንዴ ፣ ሩዝ ፣ ሳጎ ፣ ሰሞሊና ፣ ዱቄት ያሉ የተለያዩ የእህል ዓይነቶችን መውሰድ ይችላል። እንዲሁም አነስተኛ መጠን ያለው የበቆሎ እና ገብስ ሊወሰዱ ይችላሉ።

7.   አትክልት- ዝቅተኛ ፖታስየም ያላቸው አትክልትን በብዛት ሊወሰዱ ይችላሉ። ነገር ግን ከፍተኛ ፖታስየም ያላቸው አትክልቶች ከመብላቱ በፊት ፖታስየምን ማስወገድ አለባቸው። ጣዕምን ለማሻሻል የሎሚ ጭማቂ መጨመር ይቻላል።

8.    ፍራፍሬዎች- እንደ ፖም ፣ ፓፓያ፣ መንደሪን እና ቤሪ የመሳሰሉት አነስተኛ የፖታስየም ይዘት ያላቸው ፍራፍሬዎች በቀን አንድ ጊዜ ብቻ መውሰድ ይቻላል። በኩላሊት እጥበት ቀን ህመምተኞች ማንኛውንም መመገብ ይችላሉ። የፍራፍሬ ጭማቂ እና የኮኮናት ውሃን ግን መወሰድ የለበትም።

9.    ወተት እና የወተት ተዋጽኦዎች- እንደ ወተት ያሉ የወተት እና የወተት ተዋጽኦዎች ፣እርጎ እና አይብ ከፍተኛ መጠን ያለው ፎስፈረስ ስለሚይዙ አመጋገብ ላይ መጠናቸው መወሰን አለባቸው። ሌሎች አነስተኛ መጠን ፎስፈረስ ያላቸው የወተት ተዋጽኦዎች እንደ ቅቤ ፣ክሬምአይብ፣ ሪኮታ አይብ፣ ሸርቤትስ፣ ወተት የሌለበት የሰላጣ ማጣፍጫ እና የመሳሰሉትን እንደምትክ መጠቀም ይቻላል።

10.   ቀዝቃዛ መጠጦች- ጥቁር ቀለም ያላቸውን ሶዳዎች የፎስፈረስ ይዘት ከፍ ያለ በመሆኑ ከመጠቀም ይከልከሉ። የፍራፍሬ ጭማቂ ወይም የኮኮናት ውሃ ከፍተኛ የፖታስየም ይዘት ሊኖረው ስለሚችል አይወስዱ።

11.    ደረቅ ፍራፍሬዎች- ደረቅ ፍራፍሬዎች ፣ ለውዝ፣ዘቢብ፣ቴምር፣ የሰሊጥ ፍሬዎች ትኩስ ወይም ደረቅ ኮኮናት እንዲወስዱዋቸው አይመከርም።