Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

10. ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም መንስኤዎች

ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም መንስኤዎች

ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም (..) ለሕክምና አስፈሪ ና መድኃኒት የሌለው ህመም ነው። ይህ ህመም በአለም ላይ በሚያስደንቅ ፍጥነት እየጨመረ ነው። ከአስር ሰዎች መካካል አንዱ አንድ ዓይነት ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ይኖርበታል። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ የስኳር ፣ የደም ግፊት ፣ የውፍረት ፣ ሲጋራ ማጨስ እና ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን ለሥር የሰደደ ኩላሊት ህመም ተጋላጭነትን ዋና ምክንያቶች ናቸው።

ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ምንድን ነው?

ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም የሚከሰተው ኩላሊቶች ሲጎዱና ቀስ በቀስ አቅም ሲያጡ ነው። በሕክምና አማካኝነት የኩላሊት ሥራ ሊሻሻል ይችላል። ካልሆነ ግን ጉዳቱ ከአመት እስከ አመት እየባሰ ይሄዳል። የሴረም ክሬቲኒን መጠንም ቀስ በቀስ እየጨመረ ይሄዳል። የኩላሊት ተግባሩን የማከናወን አቅም ወይም ደረጃ ግሎሜሩላር ማጣሪያ መጠን ወይም ጂኤፍአር ተብሎም የሚጠራውን ከዚህ የደም ምርመራ ልናውቅ እንችላለን። የህመሙ ደረጃ መለስተኛ መካከለኛ ወይም ከባድ ተብሎ ሊከፈል ይችላል። በሽንት ውስጥ አልቡሚን መኖሩ የኩላሊት ጉዳት መከሰቱን ያሳያል። ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ቀደም ሲል ሥር የሰደደ የኩላሊት ውድቀት ተብሎ ይጠራ ነበር። ነገር ግን ውድቀት የሚለው ቃል የተሳሳተ ግንዛቤ ስለሚሰጥ ስሙ ተቀይሯል። ህመሙ መጀመሪያ ደረጃ ላይ ሲሆን የተወሰነ የኩላሊት ተግባር ይኖራል። የኩላሊት ውድቀት የሚከሰተው ህመሙ መጨረሻ ደረጃ ላይ ሲደርስ ብቻ ነው።

የመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም ምንድነው?

የመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም ወይም የመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ወደ የላቀ ደረጃ (የኩላሊት መደበኛው ተግባር የማከናወን አቅም ከ10% በታች) የሚደርስበትን ጊዜ ያመለክታል። በዚህም ጊዜ ኩላሊቶቻችን ሙሉ በሙሉ ሊደክሙ ይችላሉ። ይህም ሁኔታ የማይቀለበስ ወይም የማይመለስ ነው። በዚህም ሰዐት መድኃኒት መውሰድ ፣ አመጋገብን ማስተካከል ወይም የአኗኗር ዘይቤ ማሻሻል ህይወትን ለማቆየት በቂ አይደለም። በዚህም ምክንያት የኩላሊት እጥበት ወይም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህይወትን ለማዳን ያስፈልጋል።

ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም መንስኤ ምንድነው?

በርካታ ሁኔታዎች በኩላሊቶች ላይ ዘላቂ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ነገር ግን ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ሊያስከትሉ የሚያስችሉ ዋና ምክንያቶች የስኳር ህመምና የደም ግፊት ናቸው። እነዚህ መንስኤዎች ሥር የሰደደ የኩላሊት ችግርን ከሚያስከትሉ ህመሞች ሁለት ሶስተኛውን ይወክላሉ። የህመሙ ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው:-

1. የስኳር ህመም

የስኳር ህሙማን ከ35-40% ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመምተኞችን ያካትታሉ። በጣም የተለመደ የኩላሊት ህመም መንስኤ ነው። በግምት ከሶስት የስኳር ህሙማን አንዱ ለሥር የሰደደ ኩላሊት ህመም የመጋለጥ አቅሙ ከፍተኛ ነው።

2. ከፍተኛ የደም ግፊት

ያልታወቀ ወይም በትክክለኛው መንገድ ያልታከመ የደም ግፊት መጠን ወደ 30% ህመምተኞች የያዘ የሥር የሰደደ ኩላሊት ህመም መንስኤን ነው። በተጨማሪም ለሥር የሰደደ ኩላሊት ህመም መከሰት ምክንያት ሌላም ቢሆንም ከፍተኛ የደም ግፊት በእርግጠኝነት በኩላሊቶች ላይ ተጨማሪ ጉዳት ያስከትላል።

3. ግሎሜሮሎኔፍሪያተስ

እነዚህ ህመሞች ለሥር የሰደደ ኩላሊት ህመም መከሰት ሥስተኛ መንስኤ ናቸው። ለእብጠትን እና ለኩላሊት ጉዳት ይዳርጋሉ።

4. ፖሊሲስቲክ የኩላሊት ህመም

ይህ በጣም የተለመደ በዘር የሚተላለፍ የሥር የሰደደ ኩላሊት ህመም መንስኤን ነው። ህመሙም ተለይቶ የሚታወቀው ሁለቱም ኩላሊት ላይ በርካታ ውሃ የቋጠሩ እጢዎች ስለሚኖሩ ነው።

5. ሌሎች ምክንያቶች-

የኩላሊት እርጅና እና የደም ቧንቧ ችግር (መጥበብ) የሽንት ፍሰትን በድንጋይ ወይም በተስፋፋ ፕሮስቴት መገደብ ፣ በመድኃኒት መርዛማነት ምክንያት የሚመጣ የኩላሊት መጎዳት ፣በልጆች ላይ ተደጋጋሚ የኩላሊት ኢንፌክሽን፣ ሪፍሌክስ ኔፍሮፓቲ እና የመሳሰሉት ናቸው።