Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

5. ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች

የኩላሊት ህመሞች በሁለት ዋና ዋና ቡድኖች ይከፈላሉ እነርሱም

የውስጥ ደዌ ህመሞች: የውስጥ ደዌ ህመሞች ማለትም ፤እንደ የኩላሊት መድከም ፣ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን እና ኔፍሮቲክ ስንድረም የመሰሉጥ በኩላሊት ህክምና ስፔሻሊስት የሚታከሙ ናቸው። ከፍተኛ የኩላሊት መድከም ያጋጠማቸው ህመምተኞች ስራ የኩላሊት እጥበት እና የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያሉ ህክምናዎች ያስፈልጋቸዋል።

የቀዶ ጥገና ህመሞች፡ የኩላሊት እና የሽንት ቧንቧ የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ሃኪም እንደ የኩላሊት ጠጠር ፣ የፕሮስቴት ችግሮች እና የሽንት ቧንቧ ካንሰርን በቀዶ ጥገና፣ በኢንዶስኮፒ እና በሊቶትርሪፕሲ ያታክማሉ።

የከላሊት ስፔሻሊስት ሃኪም እና የኩላሊት እና የሽንት ቧንቧ የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ሃኪም መሃል ያለው ልዩነት?

የኩላሊት ህክምና ስፔሻሊስቶች በኩላሊት ሜዲካል ህመሞች፡ በኩላሊት እጥበት (ዲያሊሲስ) እና የኩላሊት ንቅለ ተከላ ባለሞያ ሲሆኑ የኩላሊት እና የሽንት ቧንቧ የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ሃኪም ደግሞ የቀዶ ጥገና ህመሞች የሆኑትን እንደ ጠጠር፤ እጢ፤ የፕሮስቴት እና የኩላሊት ካንሰር የሚያክም ባለሞያ ነው።

ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች

የውስጥ ደዌ

የቀዶ ጥገና

አጣዳፊ የኩላሊት መድከም

ስር ሰደድ የኩላሊት መድከም

የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን

ኔፍሮቲክ ስይንድረም

የጠጠር ህመም

የሽንት ፊኛ እና የፕሮስቴት ችግሮች

የሽንት አካላት የአፈጣጠር ችግሮች

ካንሰር

 

የኩላሊት መድከም

ጉልህ የሆነ የኩላሊት የቆሻሻ የማጣራት እና የማስወገድ፤ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ኤሌክትሮላይት ሚዛን መጠበቅ ችሎታ መቀነስ የኩላሊት መድከም ይባላል። በሴረም ክሪያቲኒን የደም ዩሪያ ናይትሮጅን መጠን መጨምር አብዛኛውን ጊዜ የኩላሊት መዳከም እና ህመምን ያመለክታል።

የኩላሊት መዳከም በሁለት ይከፍላል። እነሱም አጣዳፊ የኩላሊት መድከም እና ስር ሰደድ የኩላሊት ህመም(መዳከም) ናቸው።

አጣዳፊ የኩላሊት መድከም

በድንገት የሚከስት የኩላሊት ሰራ መቀነስ አጣዳፊ የኩላሊት መድከም ወይም አጣዳፊ የኩላሊት መጎዳት ይባላል። በአብዛኛው የአጣዳፊ የኩላሊት መድከም ታማሚዎች ላይ የሽንት መጠን መቀነስ ይታያል።እንደ አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት የፋልሲፓረም ወባ፤ ዝቅተኛ የደም ግፊት፤ የደም መበከል እና አንዳንድ መድሃኒቶች ብርቱ አጣዳፊ የኩላሊት መድከም የሚያመጡ ምክንያቶች ናቸው። በአብዛኛውን ጊዜ በትክክለኛው ህክምና የኩላሊትን የመስራት አቅም መመለስ ይቻላል።

ስር ሰደድ የኩላሊት ህመም

ቀስ በቀስ በየጊዜው የሚጨምር የማየቀለበስ ምናልባትም፤ በወራት እና በአመታት ጊዜ የኩላሊት አቅም መድከም ስር ሰደድ የኩላሊት ህመም ይባላል።በስር ሰደድ የኩላሊት ህመም ወቅት የኩላሊት የስራ አቅም ቀስ በቀስ በየጊዜው ይቀንሳል። ከረጅም ጊዜ በኋላ ኩላሊት ሙሉ ለሙሉ ስራ የሚያቆምበት ደረጃ ላይም ይደርሳል። ይህ ከፍተኛ እና ለህይወት አስጊ የሆነው ህመም የመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም ይባላል።

ስር ሰደድ የኩላሊት ህመም ዝም ያለ ለረጅም ጊዜ ሳይታወቅ ሊኖር የሚችል ህመም ነው። በመጀመሪያ ስር ሰደድ የኩላሊት ህመም ደረጃ ምልክቶች ትንሽ ሆኖ በሚታይበት ወቅት፤ በቀላሉ ህመሙን በአግባቡ የሚያመላክት አይሆንም። የተለመዱት ስር ሰደድ የኩላሊት ህመም ምልክቶች አጠቃላይ ድካም፤ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፤ ማቅለሽለሽ ማስመለስ፤ አጠቃላይ የሰውነት ማበጥ እና ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት ናቸው።ስኳር እና ከፍተኛ የደም ግፊትም ዋና ዋና የተለመዱ የስር ሰደድ የኩላሊት ህመም መነሻዎች ናቸው።

በሽንት ውስጥ የፕሮቲን መኖር ፤ከፍተኛ የሆነ የደም ውስጥ የክሪያቲኒን መጠን በአልትራሳውንድ ላይ የኩላሊት መጠን ማነስ አስፈላጊ እና ዋና የስር ሰደድ የኩላሊት ህመም የምርመራ ምልክቶች ናቸው። በደም ውስጥ የሚገኘው የክሪያቲኒን መጠን የኩላሊት ህመም መጠን ያሳያል ከጊዜ ወደ ጊዜም መጠኑ እየጨመረ ይሄዳል። ስር ሰደድ የኩላሊት ህመም የመጀመሪያ ደረጃዎች በሽተኛው ተገቢ የሆነ መድሃኒት እና የአመጋገብ ስርአቱ መስተካከል አለበት። ህመሙ ፍቱን የሆን መድሃኒት የለውም። አንድ ሰው እያረጀ ሲሄድ የኩላሊት የመስራት አቅም እየቀነሰ ይሄዳል። ቁጥጥር የማይደረግበት ከሆነ የስኳር ህመም እና የደም ግፊት የመሳሰሉ ተጓዳኝ ህመሞች ከዕድሜ ጋር ተያይዞ በፍጥነትና በሂደት ለኩላሊት ሥራ ማሽቆልቆል አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል።

የሕክምናው ዓላማ የሕመሙ ክብደት ወይም ደረጃ ቢለያይም የበሽታውን እድገት መቀነስ የተወሳሰበ ችግርን መከላከል እና ረዘም ላለ ጊዜ ታካሚውን ማቆየት ነው።

ህመሙ ወደ ከፍተኛ ደረጃ (ወደ መጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም) ሲሸጋገር 90% በላይ የኩላሊት ተግባር ይጠፋል (የደም ክሪያቲኒን አብዛኛውን ጊዜ 8-10 ሚግ/ዴሊ)

በዚህ ደረጃ ላይ የሚገኙት ብቸኛ የህክምና አማራጮች ኩላሊት እጥበት (ሂሞዲሊያሲስ እና ፐሪቶኒያል ኩላሊት እጥበት) እና የኩላሊት ንቅለ ተከላናቸው።

ኩላሊት እጥበት ኩላሊት ሥራውን ሲያቆም በሰውነት ውስጥ ሊከማቹ የሚችሉ ቆሻሻ ምርቶች እና አላስፈላጊ ፈሳሾችን ከሰውነት ለማስወገድ የማጣሪያ ሂደት ነው። ዲያሊሲስ የሥር ሰደደ የኩላሊት ህመም መድኃኒት አይደለም። የሥር ሰደደ የኩላሊት ህመም (የመጨረሻ ደረጃ የሥር ሰደደ የኩላሊት ህመም) ታማሚ የዕድሜ ልክ መደበኛ የዲያሊያሲስ ሕክምና ይፈልጋል (ኩላሊቱ በተሳካ ሁኔታ ካልተተካ በስተቀር)። ሁለት የዲያሊሲስ ዘዴዎች ሲኖሩ ሂሞዲያሊያሊስ እና ፐርሰናል ዲያሊያስ ናቸው።

ሄሞዲያሊያሊስ በስፋት ጥቅም ላይ የዋለው የኩላሊት እጥበት አየነት ነው። በሄሞዲያሊያሊስ ውስጥ ልዩ ማሽን በመጠቀም የሰውነት ቆሻሻ ምርቶች ፣ አላስፈላጊ ፈሳሾች እና ጨው ይወገዳሉ። ተዛማጅ አምቡላቶሪ የፔሪቶንያል ኩላሊት እጥበት ሌላ ዓይነት የዲያሊሲስ ዘዴ ሲሆን ያለ ማሽን እገዛ በቤት ወይም በሥራ ቦታ ሊከናወን ይችላል። የኩላሊት ንቅለ ተከላ በጣም ተስማሚ የሕክምና አማራጭ እና የመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት እጥበት ብቸኛ ፈዋሽ ሕክምና ዘዴ ነው።

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን

ማቃጠል እና ብዙ ጊዜ መሽናት ፣ በታችኛው የሆድ ውስጥ ህመም እና ትኩሳት በጣም የተለመዱ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክቶች ናቸው: በሽንት ምርመራ ውስጥ የመግል ሴሎች መገኘት ሊጠቁሙ ይችላሉ። አብዛኛዎቹ የሽንት ቧንቧ ህመም ያለባቸው ታካሚዎች፤ ለተገቢ ፀረ-ባክቴሪያ ሕክምና ጥሩ ምላሽ ይሰጣሉ።

በልጆች ላይ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ልዩ ትኩረት ይፈልጋል። በልጆች ላይ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን መዘግየት ወይም በቂ ያልሆነ ህክምና አለማድረግ፤ በታዳጊው ኩላሊት ላይ የማይመለስ ጉዳት ያስከትላል።

በተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን በሚከሰትባቸዉ ታካሚዎች ላይ የሽንት መዘጋትን ፣ የጠጠር ህመምን ፣ የሽንት መጎሳቆልን አለመመጣጠን እና የጄኒዬሪንየር ሳንባ ነቀርሳን በምርመራ ለይቶ ማከም በጣም አስፈላጊ ነው። በልጆች ላይ የሽንት መተላለፊያው ተላላፊ በሽታ እንደገና እንዲከሰት የሚያደርገው ዋናው ነገር ቬሲኮዩሬትሪክ ሪፍለክስ ነው። ቬሲኮዩሬትሪክ ሪፍሌክስ ሽንት በተቃራኒው ፤ ማለትም ከፊኛው ወደ አንዱ ወይም ወደ ሁለቱም የላይኛው የሽንት ቱቦ ወይ እስከ ኩላሊት ድረስ ወደ ኋላ የሚፈስሰው ተፈጥሮአዊ ያልተለመደ ሁኔታ ነው።

የኔፊሮቲክ ሲንድሮም

የኒፍሮቲክ ሲንድሮም የተለያዩ ምልክቶች ያጠቃልላል ፤ማለትም እንደ እብጠት (የእግር እብጠት) ፣ ከባድ ፕሮቲኖች (በቀን ከ 3.5 ግራም በሽንት ውስጥ ያለ የፕሮቲን መጠን) ፣ ሃይፖአልቡሚኔሚያ (በደም ውስጥ ያለው ዝቅተኛ አልቡሚን) እና ከፍተኛ የደም ኮሌስትሮል ደረጃዎች ናቸዉ። እንደ እነዚህ ዓይነቶቹ ታካሚዎች በመደበኛ ወይም ከፍ ያለ የደም ግፊት እንዲሁም የተለያየ የኩላሊት የመስራት አቅም በደም ውስጥ የክሬያቲንን መጠን በመለካት ሊለዩ ይችላሉ።

በሕክምና መዘግየት እና የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን በልጆች ላይ በቂ ያልሆነ ምርመራ ማደረግ፤ በማደግ ላይ ባለው ኩላሊት ላይ የማይቀለበስ ጉዳት ያስከትላል።

ይህ ህመም ለህክምናው የተለያዩ ምላሾችን ያሳያል፤ ስለሆነም የመነሻውን ምርመራ በቶሎ ማደረግ በጣም አስፈላጊ ነው። ጥቂት ህመምተኞች ከህክምናው ካቆሙ በኋላ ከምልክቶቹ ነፃ ሆነው ሊቆዩ ይችላሉ፤ ነገር ግን በአብዛኛዎቹ ህሙማን ላይ በሽታው እንደገና ይመለሳል ይህም ማለት ፣ በሕክምናው ደረጃ ላይ በመመርኮዝ በድጋሜ የሚለዋወጥ ክፍለ ጊዜ ሊኖር ይችላል ማለት ነዉ። የኒፍሮቲክ ሲንድረም ህመም ላለባቸው የታከሙ ሕፃናት የረጅም ጊዜ ውጤት በጣም ጥሩ መሆኑን መገንዘብ ጠቃሚ ነው። በተለመደው የኩላሊት ተግባር ጤናማ ኑሮን ይመራሉ።

የኩላሊት ጠጠር

የኩላሊት ጠጠር የተለመደ እና ዋና የኩላሊት ችግር ነው። ኩላሊት፣ የላይኛው የሽንት ቱቦ፣ የሽንት ፊኛ በብዛት ጠጠር የሚጊኝባቸው ቦታዎች ናቸው። የተለመዱ የኩላሊት ጠጠር መኖር ምልክቶች የምንላቸው ጠንካራ የሆነ የህመም ስሜት፣ ማቅለሽልሽ፣ ማስመለስ፣ ከሽንት ጋር የደም መቀላቀል እና የመሳሰሉ ናቸው። ነገር ግን አንዳንድ ለረጅም ጊዜ የኩላሊት ጠጠር ያለባቸው ህመምተኞች ምንም አይነት ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ።

አብዛኛውን ጊዜ፤ አልትራሳውንድ እና የሆድ ራጅ የጠጠር በህመሙን ለመመርመር የምንጠቅማቸው ምርመራዎች ናቸው። አብዛኛው መጠኑ አነስተኛ የሆነ ጠጠር እንዲሁ በተፈጥሮ ፈሳሽ ነገርን አብዝቶ በመውሰድ ብቻ ከሽንት ጋር ተቀላቅሎ ይወጣል።

ነገር ግን ጠጠሩ ተደጋጋሚ ከፍተኛ የሆነ ህመም፣ ተደጋጋሚ ኢንፌክሽን፣ የሽንት ቧንቧ መዝጋት ወይም ኩላሊት ላይ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ ሊወገድ ይገባል። ጥሩ የምንለው የጠጠር ማስውገጃ መንገድ እንደ ጠጠሩ መጠን፣ ቦታ እና አይነት ይወሰናል። ዋና ዋና የጠጠር ማስወገጃ መንገዶች የምንላቸው ሊቶትሪፕሲ፣ ኢንዶስኮፕ እና ክፍት ቀዶ ጥገና ናቸው።

የኩላሊት ጠጠር 50 እሰከ 80 በመቶ ተደጋግሞ የመከሰት አቅም ስላለው ወደ ሰውነት የሚገባን ፈሳሽ ነገር መጨመር የአመጋገብ ልምድን ማስተካክል እና በየጊዜው ክትትል ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው።

የፕሮስቴት ህመም

የፕሮስቴት እጢ በወንዶች ላይ ብቻ የሚገኝ ዕጢ ነው። ከሽንት ፊኛ በታች የታችኛው የሽንት ቱቦ ዙሪያ የሚገኝ ዕጢ ነው። የፕሮስቴት ዕጢ ከ50 አመት ዕድሜ በኋላ በመጠን እያደገ ይመጣል። መጠኑ ያደገ የፕሮስቴት ዕጢ የታችኛውን የሽንት ቱቦ በመጫን የሽንት አወጋገድ ላይ ችግር ይከስታል፤ ይህ ሁኔታ በተለይም እድሜ በገፉ ወንዶች ላይ ይስተዋላል።

ዋና ዋና የፕሮስቴት እጢ ምልክቶች የምንላቸው፤የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት (በብዛት በመኝታ ሰዓት) እና ሽንት ሸንተው ከጨረሱ በኋላ ማንጠባጠብ ናቸው። በፊንጢጣ በኩል ጣትን በመስደድ የሚደረግ ምርመራ እና አልትራሳውንድ ዋነኛ የሆኑ የምርመራ መንገዶች ናቸው። ከአነስተኛ እስከ መካከለኛ የህመም ምልክቱ ያላቸው በርካታ ህመምተኞች ለረጅም ጊዜ በመድሃኒት ሊታከሙ ሲችል ከፍተኛ የሆነ የህመም ስሜት ያላቸው የፕሮስቴት ዕጢያቸው በጣም ትልቅ የሆኑ ደግሞ በኢንዶስኮፒ ዕጢው ሊወገድላቸው ይችላል።