Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

ስለ ደራሲው

ዶ/ር እሴተ ጌታቸዉ ኤም.ዲ.,ጠቅላላ ሐኪም

ዶ/ር እሴተ ጌታቸው የህክምና ዲግሪያቸውን በማዩንግሰንግ ሜዲካል ኮሌጅ በ2010 ዓ.ም አግኝተዋል። የኢትዩጵያን ኪድኒ ኬር መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ፤ከ2010 እስከ አሁን ድረስ በኩላሊት እጥበት ላይ እየሰሩ ይገኛሉ። ኢትዩጵያን ኪድኒ ኬር ያቋቋሙት ኢትዩጵያ ላይ ያለውን የኩላሊት ህመም ችግር ላይ ለመስራት ነው፤ከድርጅቱ ሥራዎች መካከል አንዱ ህብረተሰቡን ማስተማር አንዱ እንደመሆኑ መጠን ይህን ሴቭ ዮር ኪድኒ የሚባልው የኢንጊልዘኛ መጽሐፍ ከበጎፈቃደኛ የህክምና ተማሪዎች እና ሌሎች ጋር በመተባበር ወደ አማርኛ ተርጉመውታል። ይህ መጽሐፍ ህብረተሰቡን ስለኩላሊት ህመም ግንዛቤ ያስጨብጣል ተብሎ ይታሰባል። ወደ ፊት ወደ ሌሎች የኢትዮጵያን ቋንቋዎች ለመተርጎም ታቅዷል።

 

 

ዶ/ር ሳንጃይ ፓንዲያ ኤም ዲ ዲንቢ (ኒፍሮሎጂ) ፣ የኩላሊት ሐኪም

ዶክተር ሳንጃይ ፓንዲያ የኩላሊት ህክምና ባለሙያ ሲሆኑ በራጅኮት (ጉጂራት - ህንድ) ውስጥ ያገለግላሉ። ከኤም. ፒ. ሻህ ሜዲካል ኮሌጅ (M.D) የህክምና ዶክተር (በውስጥ ደዌ ህክምና) ጀማናጋር (ጉጂራት) እ.ኤ.አ. በ 1986 እና (DNB) የኩላሊት ህክምና የኩላሊት ህመም እና የምርምር ማዕከል ተቋም አህመድባድ በ 1989 አግኝተዋል። እ.ኤ.አ. ከ 1990 ጀምሮ በራጅኮት (ጉጂራት) ህንድ. በኩላሊት ህክምና ልምድ እያገለገሉ ይገኛሉ።

ዶክተር ፓንዲያ በኩላሊት ህመም ትምህርት ውስጥ በንቃት ይሳተፋል የኩላሊት መጽሐፍ ለህመምተኞች በእንግሊዝኛ ፣ ሂንዲ ፣ ጉጃራቲ እና ኩቱቺ ቋንቋዎች ጽፈው አቅርበዋል። “የኩላሊት ትምህርት ፋውንዴሽን” በዶክተር ፓንዲያ የተቋቆመ ሲሆን ተልዕኮው ለብዙ ሰዎች የኩላሊት ህመም መከላከል እና እንክብካቤን ግንዛቤን ለማሰራጨት ነው።

ከተለያዩ የአለም ክፍሎች በተውጣጡ የኩላሊት ሐኪሞች ቡድን ትብብር የተለያዩ ለኩላሊት ህመምተኞች የትምህርት መጽሐፍት ከ38 በሚበልጡ ቋንቋዎች ተዘጋጅተው ቀርበዋል።

የተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሰዎች እና የኩላሊት ህመምተኞች ለመርዳት www.KidneyEducation.com ድረ ገጽ በዶክተር ፓንዲያ እና የእሱ ቡድን አባሎች ተመስርቶል። ይህ ድረ ገጽ በነፃ 230 ገጽ የኩላሊት መጻሕፍን ከ38 በሚበልጡ ቋንቋዎች ለማውረድ ያስችላል። ይህ የኩላሊት ድረ ገጽ በጣም ታዋቂ እና ከ90 ሚሊዮን በላይ ምልከታዎችን በመጀመሪያዎቹ 130 ወሮች ውስጥአግኝቶል።