Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

6. ስለ ኩላሊት ህመሞች ትክክል ያልሆኑ አመለካከቶች እና እውነታዎች

የተሳሳቱ አመለካከቶች፡ ሁሉም የኩላሊት ህመሞች አይድኑም።

እውነታ፡ ሁሉም የኩላሊት ህመሞች አይድኑም ማለት አይቻልም። በቶሎ ከታወቀ እና ከታከሙ ግን አብዛኞቹ የኩላሊት ህመሞች ሊድኑ ይችላሉ። አብዛኛዉን ጊዜ በቶሎ መታወቁ እና መታከሙ ወደ ባሰ ደረጃ እንዳይሄድ እና ሂደቱም እንዲዘገይ ይረዳል።

የተሳሳቱ አመለካከቶች፡ አንዷ ኩላሊት ደከመች ማለት ሁለቱም ተበላሽቷል ማለት ነው።

እውነታዉ፡ የኩላሊት ስራ ማቆም የምንለው ሁለቱም ኩላሊቶች ሲደክሙ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ታማሚዎች አንድ ኩላሊታቸው ሙሉ ለሙሉ ድክሞም ቢሆን፤ ምንም አይነት ምልክት እና ችግር አያሳይም። በደም ውስጥ ያለው የዩሪያ ናይትሮጅን እና ክሪያቲኒን ንጥረ ነገር መጠንም በጤናማ ምጣኔ ላይ ሊገኝ ይችላል። ነገር ግን ሁለቱም ኩላሊቶች ሲዳከሙ በደም ዉስጥ ያለው የዩሪያ ናይትሮጅን እና ክሪያቲኒን መጠን በመጨመር የኩላሊት ስራ መዳከምን ሊያመላክት ይቸላል።

የተሳሳቱ አመለካከቶች፡ በኩላሊት ህመም ጊዜ የሰውነት ማበጥ የኩላሊት ስራ ማቆም ያሳያል።

እውነታዉ፡ በአንዳንድ የኩላሊት ህመሞች ጊዜ የሰውነት ማበጥ ቢኖርም እንኳን የኩላሊት የሥራ አቅም ጤናማ ሊሆን ይችላል ለምሳሌ ኔፍሮቲክ ሲንድረም። አንድ ሰው የሰውነት ማበጥ ሲከሰት መረዳት ያለበት ነገር፤ የሰውነት የፈሳሽ ስርዓት እንደተዛባ ነው። ይህ እንዲከሰት ከሚያደርጉ ህመሞች መሃከል ደግሞ የኩላሊት ህመም አንዱ እና የተለመደው ነው።

የተሳሳቱ አመለካከቶች፡ የሰውነት ማበጥ በሁሉም የኩላሊት መድከም ህመምተኞች ላይ ይኖራል።

እውነታዉ፡ የሰውነት ማበጥ በአብዛኛው የኩላሊት መድከም ህመምተኞች ላይ ይኖራል ነገር ግን ሁሉም ይታያል ማለት አይደለም። አንዳንድ ታማሚዎቸ ከፍተኛ ደረጃ የኩላሊት መድከም ተከስቶባቸዉ እንኳን ምንም አይነት የሰውነት እብጠት አይኖርባቸውም። በመሆኑም የሰውነት እብጠት አለመኖር የኩላሊት መድከም አለመኖርን የግድ አመላካች አይሆንም።

የተሳሳቱ አመለካከቶች፡ ሁሉም የኩላሊት ታማሚዎች ብዙ ዉሃ መጠጣት አለባቸው።

እውነታ፡ የሽንት መጠን መቀነስ የብዙ የኩላሊት በሽታ አይነቶች እና ምልክት ነው። ስለዚህ በእንደዚህ አይነት ታማሚዎች ላይ የውሃ መጠንን መገደብ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ታማሚዎቹ ከኩላሊት ጠጠር እና ከሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ህመም የተጠቁ እና የኩላሊት አውማቸው ጤነኛ ከሆነ ብዙ ውሃ እንዲጠጡ ይመከራሉ።

የተሳሳቱ አመለካከቶች፡ ምንም አይነት የህመም ስሜት አይሰማኝም ስለዚህ የኩላሊት ችግር ያለብኝ አይመስለኝም።

እውነታዉ፡ አብዛኞች ታማሚዎች ምንም አይነት የህመም ስሜት በመጀመሪያዎቹ የኩላሊት በሽታ ደረጃዎች ላይ አያሳዩም። ጤናማ ያልሆኑ የላብራቶሪ ውጤቶች ብቻ ግን የበሽታው አመላካች ሊሆኑ ይችላሉ።

የተሳሳቱ አመለካከቶች፡ ምንም አይነት የህመም ስሜት አይሰማኝም ስለዚህ የኩላሊት በሽታዬን ህክምና ባቋርጥ ችግር አይኖረውም።

እውነታዉ፡ አብዛኛው የስር ሰደድ የኩላሊት ህመም ታማሚዎች ከተገቢው የህክምና ክትትል ጋር ምንም አይነት የህመም ስሜት ላይሰማቸው ይችላል በዚህ ጊዜ የታዘዘላቸውን መድሃኒት እና የአመጋገብ ዘይቤ ሊያቋርጡ ይችላሉ። በስር ሰደድ የኩላሊት በሽታ መድሃኒት ከተቋረጠ እጅግ በጣም አደገኛ ሲሆን በጣም የፈጥነ የኩላሊት አቅም እንዲቀንስ በማድረግ ለኩላሊት አጠባ ወይም ለኩላሊት ንቅለተከላ ሊያደርግ ይችላል።

የተሳሳቱ አመለካከቶች፡ የደም ዉስጥ ክሪያቲኒን መጠን ትንሽ ጨምሯል ነገር ግን ምንም አይነት የህመም ስሜት ስለሌለኝ ምንም የሚያሳስብ አይደለም።

እውነታ፡ የደም ውስጥ ክሪያቲኒን መጠን በትንሹም መጨመር የኩላሊት ችግር ምልክት ሊሆን ይችላል፤ ተጨማሪ ይሆነ ክትትል ያሻዋል። ብዙ አይነት የኩላሊት በሽታዎች ኩላሊትን ሊጎዱ ስለሚችሉ በቶሎ የኩላሊት ህክምና ስፔሻሊስት ማናገር ተገቢ ነው። በቀጣዩ አንቀፅ በደም ዉስጥ ያለ የክሪያቲኒን መጠን መጨመር (በትንሹም ቢሆን) ከተለያዩ የስር ሰደድ የኩላሊት በሽታ ደረጃዎች ጋር እንደሚያያዝ እንመለከታለን።

የመጀመሪያ ደረጃ የስር ሰደድ የኩላሊት ህመም አብዛኛውን ጊዜ ምልክት አያሳይም። በዚህም ጊዜ የደም ውስጥ የክሪያቲኒን መጠን መጨመር ብቸኛ ምልክት ሊሆን ይችላል። የደም ውስጥ የክሪያቲኒን መጠን 16 ሚግ/ዲሊ ደረሰ ማለት ኩላሊት የሥራ የመስራት አቅሙን ግማሽ በግማሽ አጥቷል ማለት ነው፤ ይህ ደግሞ በጣም አስጊ ሁኔታ ነው። የስር ሰደድ የኩላሊት ህመም በቶሎ መታወቅ እና ተገቢውን ህክምና መጀመር በዚህ ደረጃ እጅግ አመርቂ ውጤት ያስገኛል። በኩላሊት ህክምና ስፔሻሊስት የታገዘ ህክምና ማግኘት ደግሞ የቀረውን የኩላሊት መስራት አቅም ለረጅም ጊዜ ለማቆየት ይረዳል። የክሪያቲኒን መጠኑ እስከ 50ሚግ/ዴሊ ከደረሰ ደግሞ ከ 80% በላይ የሆነ የኩላሊት የመስራት አቅም ጠፍቷል ማለት ነው። ይህ መጠን ከፍተኛና አስጊ የሆነ የኩላሊት አቅም ማጣትን ያሳያል። ተገቢው ህክምናም በዚህ ጊዜ የቀረው የኩላሊት አቅምን ለማቆየት ይረዳል። ነገር ግን ይህ ደረጃ የዘገየ ስርሰደድ የኩላሊት ህመም ደረጃ ሲሆን ጥሩ የሆነ የህክምና ውጤት የማግኘት እድልም የለውም። የክሪያቲኒን መጠኑ 10ሚግ/ዴሊ ከሆነ ደግሞ 90% የሆነ የኩላሊት የመስራት አቅም ጠፍቷል ማለት ነው። ይህም የመጨርሻ ደረጃ የስር ሰደድ የኩላሊት ህመም ነው። ለዚህ የስር ሰደድ የኩላሊት ህመም ደረጃ በመድሃኒት ህክምና የማግኘት እድሉ አልፏል። አብዛኞች ታማሚዎች የኩላሊት እጥበት (ዲያሊሲስ) ወይም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያስፈልጋቸዋል።

የተሳሳቱ አመለካከቶች፡ የኩላሊት አጠባ አንዴ በኩላሊት መድከም ታማሚ ላይ ከተሰራ በቋሚነት መሰራት ይኖርበታል።

እውነታዉ፡ የኩላሊት እጥበት፤ ጊዜያዊ ይሁን ቋሚ የሚለዉን የሚወስኑ ብዙ ገፊ ምክንያቶች አሉ።

አጣዳፊ የኩላሊት መድከምና አጣዳፊ የኩላሊት መጎዳት ጊዜያዊ እና ተቀልባሽ የሆኑ የኩላሊት መድከም ናቸው። አንዳንድ አጣዳፊ የኩላሊት መድከም ታማሚዎች የኩላሊት እጥበት እገዛ የሚያስፈልጋቸው ለአጭር ጊዜ ብቻ ነው። ተገቢው ህክምና እና ከጥቂት የኩላሊት እጥበት እገዛዎች በኋላ ኩላሊታቸው ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራዉ ይመለሳል። ቋሚ የኩላሊት እጥበት ያስፈልጋል ብሎ በማሰብ ብቻ የኩላሊት እጥበት እገዛን ማዘግየት ለህይወት እጅጉን አስጊ ሊሆን ይችላል።

ስር ሰደድ የኩላሊት ህመም ደረጃ በደረጃ የሚብስ የማይመለስ የኩላሊት መድከም ነው። ከፍተኛ ደረጃ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም መደበኛ የህይወት ዘመን የኩላሊት እጥበት አልያም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያስፈልገዋል።

የተሳሳቱ አመለካከቶች፡ የኩላሊት አጠባ የኩላሊት መድከም ህመምን ያድናል።

እውነታዉ፡ ዲያሊሲስ የኩላሊት መድከም ህመሙን አያድንም። ዲያሊሲስ በሌላ ስሙ የኩላሊት ተተኪ ህክምና ይባላል። እጅግ ውጤታማና ህይወት ታዳጊ የሆነ የሰውነት ቆሻሻን አላስፈላጊ የሰውነት ፈሳሽን የሚያስወግድ እና የሰውነት ንጥረ ነገሮችን መጠን ለመቆጣጠር የሚረዳ የኩላሊት መድከም ህክምና ነው።

አጣዳፊ የኩላሊት መድከም እና አጣዳፊ የኩላሊት መጎዳት ጊዚያዊ እና ተቀልባሽ የሆኑ የኩላሊት መድከም ናቸው። አንዳንድ አጣዳፊ የኩላሊት መድከም ታማሚዎች የኩላሊት እጥበት እገዛ የሚያስፈልጋቸው ለአጭር ጊዜ ነው። ተገቢው ህክምና እና ከጥቂት የየኩላሊት እጥበት እገዛዎች በኋላ ኩላሊታቸው ሙሉ ለሙሉ ይድናል። እድሜ ልክ የኩላሊት እጥበት ያስፈልጋል ብሎ በማሰብ የየኩላሊት እጥበት እገዛን ማዘግየት ለህይወት እጅጉ አስጊ ሊሆን ይችላል። ስር ሰደድ የኩላሊት ህመም ደረጃ በደረጃ የሚብስ የማይቀለበስ መድከም ነው። ከፍተኛ የሆነ ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም መደበኛ የሆነ የህይወት ዘመን የኩላሊት እጥበት ወይም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያስፈልገዋል።

የተሳሳቱ አመለካከቶች፡ የኩላሊት እጥበት የኩላሊት መድከም ህመምን ያድናል።

እውነታዉ፡ የኩላሊት ዕጥበት የኩላሊት መድከም ህመሙን አያድንም። የኩላሊት እጥበት በሌላ ስያሜዉ የኩላሊት መተኪያ ህክምና ተብሎ ይጠራል። እጅግ ዉጤታማ እና ህይወት አድን የሰውነት ቆሻሻን አላስፈላጊ የሰውነት ፈሳሽን የሚያስወግድ ፣ የሰውነት ንጥረ ነገር መጠን እና አሲዳማ መረበሽን ለመቆጣጠር የሚረዳ የኩላሊት መድከም ህክምና ነው። በአንድ ሰው አካል ውስጥ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ንጥረ ነገሮች ከተከማቹ ለሞት ሊዳርጉ ይችላሉ። የኩላሊት እጥበት ኩላሊት በመድከሟ መወጣት ያልቻለችውን ስራ ይሰራል። የኩላሊት ዕጥበት ከፍተኛ የሆነ የኩላሊት መድከም ተከሰተባቸዉ ሰዎችን እድሜ ጠብቆ ያቆያል።

የተሳሳቱ አመለካከቶች፡ ለኩላሊት ንቅለ ተከላ ጊዜ አንድ ሰው ኩላሊቱን ለተቃራኒ ፆታ መስጠት ወይም መቀበል አይችልም።

እውነታዉ፡ ወንድም ሴትም ኩላሊታቸውን ለተቃራኒ ፆታ መስጠት ወይም ከተቃራኒ ፆታ መቀበል ይችላሉ። የኩላሊት ባህሪ አሰራር እና ሁኔታ በሁለቱም ፆታ ተመሳሳይ ነው።

የተሳሳቱ አመለካከቶች፡ የደም ግፊቴ መጠን የተስተካከለ ስለሆነ የከፍተኛ ደም ግፊት መድሃኒትን መውሰድ የለብኝም። መሃኒቶቹን ባልውስድም ጤነኛ ነኝ ስለዚህ መድሃኒቱን ለምን እውስዳለው?

እውነታዉ፡ ብዙ የከፍተኛ የደም ግፊት ታማሚዎች የደም ግፊት መጠናቸው ሲስተካክል ምንም አይነት ምልክት ስለሌላቸው እና ያለ መድሃኒታቸው ጤነኛ ነን ብለው ሲያስቡ መድሃኒታቸው ያቋርጣሉ። ነገር ግን በቁጥጥር ስር ያልሆነ የከፍተኛ የደም ግፊት ድንገተኛ ገዳይ ነው በረጅም ጊዜም እንደ የልብ ድካም፣ የኩላሊት መድከም እና ስትሮክ ያሉትን ከፍተኛ የሆኑ ችግሮች ሊያመጣ ይችላል። ስለዚህ የሰውነት ወሳኝ አካላትን ለመጠበቅ ምንም አይነት /ህመም/ምልክት/ ባይኖርም እንኳን የታዘዘልን መድሃኒት በአግባቡ መውሰድ እና የደም ግፊታችን እየተከታተሉ መቆጣጠር ይጠበቅብናል።

የተሳሳቱ አመለካከቶች፡ ወንዶች ብቻ በእግራቸው መሃል ባለው ከረጢት ኩላሊት አላቸው።

እውነታዉ፡ ለወንድም ለሴትም ኩላሊት የሚገኘው በላይኛው እና በኋለኛው የሆድ ክፍል ሲሆን ተመሳሳይ ቅርፅ፣ መጠን እና የስራ ድርሻ አላቸው። በወንዶች ዋና የሆነ የመራቢያ አካል የሆነው ቆለጥ በእግር መሀከል በሚገኘው ከረጢት ውስጥ ይገኛል።