Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

4. የኩላሊት ህመሞች ምርመራዎች

ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም በቀላሉ የማይድን ሲሆን ካልታከመ ደግሞ ወደ መጨረሻው የኩላሊት ህመም ሊያመራም ይችላል። በቀደመው ምዕራፍ ላይ እንደተብራራው ፣ ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ያለበት ሰው፤ ምንም አይነት ምልክት ላይታይበት ይችላል ስለሆነም የኩላሊት ችግር በተጠረጠረ ቁጥር አስቸኳይ ምርመራ ማካሄድ በእጅጉ ይመከራል።

ኩላሊቱን ማን መመርመር አለበት? ለኩላሊት ችግር የመጋለጥ እድሉ ከፍተኛ የሆነ ማነው?

ማንኛውም ሰው የኩላሊት ችግር ሊያጋጥመው ይችላል፤ ነገር ግን የሚከተሉት የጤና ችግሮች ያሉት ሰው ላይ አደጋው ከፍ ያለ ነው፤

  • የኩላሊት ህመም ምልክቶች
  • የስኳር ህመም
  • ለመቆጣጠር አስቸጋሪ የሆነ የደም ግፊት
  • በኩላሊት ህመም የስኳር ህመም እና የደም ግፊት የታመመ የቤተሰብ አባል ያለው ሰው
  • የረጅም ጊዜ የትምባሆ ተጠቃሚነት ሰለባ መሆን ከመጠን በላይ ውፍረት
  • አዛውንቶች ( 60 ዓመት ዕድሜ በላይ)
  • ለረጅም ጊዜያት ያክል የሕመም ማስታገሻዎችን መውሰድ ፤ ለምሳሌ ኢስ ትሮይድ ያልሆኑ ፀረ-ህመም መድኃኒቶች ለምሳሌ (ኢቡፕሮፌን ፣ ናፕሮክ ሶን)
  • ከትውልድ ጊዜ ጀምሮ አብሮት የኖረ የሽንት ቧንቧ ችግር መኖር፤

እንደ እነዚህ ባሉ ከፍተኛ ተጋላጭ የሆኑ ግለሰቦች ላይ የሚደረግ ምርመራ ቀደም ብሎ ለኩላሊት ህመምን ለመለየት እና የህክምና ክትትል ለመጀመር ይረዳል።

የኩላሊት ችግሮችን እንዴት ለይቶ ማወቅ ይቻላል? በመደበኛነት ምን ዓይነት ምርመራዎች ይደረጋሉ?

የተለያዩ የኩላሊት ችግሮችን ለመመርመር ሐኪሙ ዝርዝር ታሪክ ይወስዳል። ሰውን በጥልቀት ይመረምራል የደም ግፊቱን ይፈትሻል። ከዚያም ተገቢ ምርመራዎች እንዲደረጉ የሚያዝ ይሆናል። በመደበኛነት የሚከናወን እና በጣም ጠቃሚ የሆነዉ ምርመራ፤ የሽንት ምርመራን ፣ የደም ምርመራን እንዲሁም የራዲዮሎጂ ምርመራዎችን ያካትታል።

1. የሽንት ምርመራ

የተለያዩ ዓይነት የሽንት ምርመራዎች የተለያዩ የኩላሊት በሽታ ዓይነቶችን ለይቶ በዝርዝር ለማወቅ ጠቃሚ ፍንጮችን ይሰጣሉ።

መደበኛ የሽንት ምርመራ

  • ቀላል ዋጋ ተመጣጣኝ እና በጣም ጠቃሚ የምርመራ አይነት ነው
  • መደበኛ የሽንት ምርመራ ውጤት በኩላሊት ላይ ችግር እንዳለ ፍንጭ ሊሰጠን ይችላል ነገር ግን ውጤቱ ችግር ባያሳይም አንድ ሰው የኩላሊት ህመም የለበትም ለማለት አያስችለንም
  • በሽንት ውስጥ የፕሮቲን መኖር በተለያዩ የኩላሊት ህመም ላይ ይሥተዋ ላል፤ በመሆኑም በፍጹም ቸል ሊባል አይገባዉም
  • በሽንት ውስጥ የፕሮቲን መኖር የመጀመሪያ እና ብቸኛው ሥር የሰደደ የኩ ላሊት ህመም (የልብ ህመምም ሊሆን ይችላል) የማስጠንቀቂያ ምልክት ሊሆን ይችላል
  • በሽንት ውስጥ ነጭ የደም ሴሎች መኖር የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን (UTI) መኖርን ሊያመለክት ይችላል
  • የፕሮቲን እና የቀይ የደም ሴሎች (አር..) መኖር የኩላሊት ብግነት በሽታ መኖሩን አመላካች ነዉ

ሌሎች የሽንት ምርመራዎች

  • 24 ሰዓት የሽንት ምርመራ፦ የኩላሊት ህመም ላለባቸው ህሙማን፤ በሽንት በኩል የጠፋውን ፕሮቲን ትክክለኛ መጠን ለማወቅ ይህ ዓይነቱ ምርመራ አስፈላጊ ነው። ይህ ምርመራ የYህመሙን ክብደት እንዲሁም በፕሮቲን መጥፋት ምክንያት የሕክምና ተጽዕኖ ደረጃን ለመገምገም ጠቃሚ ነው።
  • የባክቴርያ እድገት ምርምር ፦ ይህ ምርመራ (ዩቲአይ) የተባለውን የሽንት ቧንቧ የፈጠረውን ባክቴሪያ ዓይነት በተጨማሪም ለሕክምናው የአንቲባዮ ቲክስ ምርጫን በተመለከተ ጠቃሚ መረጃ ይሰጣል።
  • አሲድ ፋስት ባሲላት የሽንት ምርመራ፡- ይህ ምርመራ የሽንት ቧንቧዎ ችን ነቀርሳ ለመመርመር ጠቃሚና አስፈላጊ ነው።

2. የደም ናሙና ምርመራዎች

የተለያዩ የኩላሊት ህመሞችን በተገቢ ሁኔታ ለመለየት የተለያዩ የደም ናሙና ምርመራ ሂደቶች እጅጉን ወሳኝ ናቸው።

  • ክሬቲኒን እና ዩሪያ

በደም ውስጥ የክሬቲንና ዩሪያ መጠን የኩላሊትን ጤንነት ደረጃ ያንፀባርቃሉ። ክሬቲኒን እና ዩሪያ በተለምዶ በኩላሊት በኩል ከደም የሚወገዱ ሁለት ተረፈ ምርቶች ናቸው። የኩላሊት ሥራ በሚቀዘቅዝበት ጊዜ የክሬቲን እና የዩሪያ የደም መጠን በአንጻሩ ይጨምራል። የሴረም ክሪያትኒን መደበኛ መጠን ከ 0.9 እስከ 1.4 ./ዲሊ ሲሆን የደም ዩሪያ ናይትሮጂን መደበኛ መጠን ከ 20 እስከ 40 ./ዲሊ ነው። ከዩሪያ ናይትሮጂን ጋር ሲነፃፀር የክሬቲኒን መጠን ለኩላሊት ተግባር የበለጠ አስተማማኝ አመልካች ነው።

  • ሄሞግሎቢን

ኩላሊታችን ሄሞግሎቢንን የያዙ ቀይ የደም ሴሎችን ለማምረት ወሳኝ የሚባል የሰዉነታችን ክፍል ነዉ። ሄሞግሎቢን ዝቅተኛ በሚሆንበት ጊዜ የደም ማነስ ይከሰታል። ደም ማነስ የሥር ሰደድ የኩላሊት ህመም የተለመደ ምልክት ነው። ሆኖም የደም ማነስ በሌሎች ህመሞች ውስጥም ቢሆን በጣም በተደጋጋሚ ሊከሰት ይችላል። ስለዚህ የደም ማነስ ለኩላሊት ህመሞች የተለየ ምልክት ተደርጎ አይወሰድም።

ሌሎች የደም ናሙና ምርመራዎች

በኩላሊት ህመምተኞች ላይ በተደጋጋሚ የሚከናወኑ የተለያዩ የደም ናሙና ምርመራዎች የሚከተሉት ናቸዉ።የደም ስኳር ፣ የደም ፕሮቲን ፣ ኮሌስትሮል ፣ ንጥረ ነገሮች (ሶድየም ፣ ፖታሲየም እና ክሎራይድ) ፣ ካልሲየም ፣ ፎስፈረስ ፣ ቢካርቦኔት ኤስኦ ታይተር ወዘተ።

3. የራዲዮሎጂ ምርመራዎች

  • የኩላሊት አልትራሳውንድ

የኩላሊት አልትራሳውንድ ቀላል ፣ ጠቃሚ ፣ ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ (የጨረር ተጋላጭነት የሌለው) ምርመራ ነው። ስለ ኩላሊት መጠን በተጨማሪም ዕጢዎች እና ጠጠሮች መኖር አለመኖራቸዉን የመሳሰሉ ጠቃሚ መረጃዎችን ይሰጣል። አልትራሳውንድ ከዚህ በተጨማሪም፤ በሽንት ቧንቧው ውስጥ ያለው የሽንት ፍሰት መዘጋት አለመዘጋቱን መለየት ይችላል። በሥር ሰደድ የኩላሊት ህመም ወይም (ኩላሊት ድክመት) ደረጃ ላይ ሁለቱም ኩላሊት መጠናቸው አነስተኛ ሆኖ ሊገኝ ይችላል።

  • የሆድ ራጅ

ይህ የምርመራ ዓይነት በሽንት ቧንቧ ስርዓት ውስጥ ጠጠሮች ከተከሰቱ ለመመርመር ጥቅም ላይ ይውላል።

  • የውስጥ የደም ቧንቧ ዩሮግራፊ

የውስጥ የደም ቧንቧ ዩሮግራፊ ልዩ የራጅ ምርመራ ነው። በዚህ ምርመራ ውስጥ ቀለም (በራጅ ዉጤቶች ላይ ሊታይ የሚችል ፈሳሽ) የያዘ የሬዲዮ አዮዲን በክንድ በኩል ወደ አንድ የደም ሥር ውስጥ ይገባል። ይህ ቀለም ከዚያ በኋላ በኩላሊቱ ውስጥ በማለፍ በሽንት በኩል ይወጣል። ይህ መላውን የሽንት ክፍልን በዓይነ ሕሊናዎ እንዲታይ ያስችላል። እንደ ጠጠር ፣ አንዳች እክል ፣ ዕጢ ፤ ያልተለመዱ እና በኩላሊት መዋቅር እና ተግባር ውስጥ ያሉ ሌሎች ችግሮችን ጭምር ሊገልጽ ይችላል።

ደረጃው በገፋ በሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ውስጥ ፤ የውስጥ የደም ቧንቧ ዩሮግራፊ ብዙውን ጊዜ አይመከርም፤ ምክንያቱም በመርፌ የተወጋው ቀለም ቀድሞውኑ በደንብ የማይሠራውን ኩላሊት ሊጎዳዉ ይችላል እና ነዉ። በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት ይህ ምርመራ አይመከርም። አልትራሳውንድእና ሲቲ ስካንበስፋት በመገኘታቸው ምክንያት ይህ ምርምራ ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ አይውልም።

  • ቮይዲንግ ሲስቶዩሬትሮግራም

ይህ ምረመራ በልጆች ላይ የሚመጣን የሽንት ቧንቧ ችግር የሚያሳይ ምርመራ ነው።በዚህ ምርመራ ውስጥ ቀለም (በራጅ ዉጤቶች ላይ ሊታይ የሚችል ፈሳሽ) የያዘ የሬዲዮ አዮዲን ይገባ እና ሽንት እንዲሸና ይደረጋል ከዚያ ራጅ ይነሳል። ይህ የሽንት ወደኋላ የመመለስ ህመምን ያሳያል።

  • ሌሎች ምርመራዎች

ሲቲ ስካን ፣የኩላሊት ደም ሥር አልትራሳውንድ፣ሬድዮ ኒኩለር ጥናት፣አንጂዮግራፊ የመሳሰሉት።

የኩላሊት ባዮፕሲ

የተወሰኑ የኩላሊት ብግነት ህመም አና የኩላሊት የደም ትቦዎች ህመም ወዘተ ያሉ የተወሰኑ የኩላሊት ህመሞችን ለመለየት ጠቃሚ ምርመራ ነው።

የኩላሊት ባዮፕሲ ምንድን ነው?

በኩላሊት ባዮፕሲ ወቅት አንድ ትንሽ የኩላሊት ቁራጭ በመርፌ ተወስዶ በአጉሊ መነጽር ምርመራ ይደረጋል። የኩላሊት ባዮፕሲ የአንዳንድ የኩላሊት ህመሞችን ትክክለኛ መንስኤ ይመረምራል።

የኩላሊት ባዮፕሲ መቼ ይመከራል?

በተወሰኑ የኩላሊት ህመሞች ውስጥ እንኳን ዝርዝር ታሪክ ፣ የአካል ምርመራ እና መደበኛ ምርመራዎች ትክክለኛውን መንሰዔ መለየት አይችሉም። በእንደዚህ ዓይነት ህመምተኞች ውስጥ የኩላሊት ባዮፕሲ ተጨማሪ መረጃ ሊሰጥ ይችላል። ይህም ትክክለኛውን ምርመራ ሊያሳውቀን ይችላል።

የኩላሊት ባዮፕሲ እንዴት ይረዳል?

የኩላሊት ባዮፕሲ የተወሰኑ ያልታወቁ የኩላሊት በሽታዎች ልዩ መንሰዔ ያወጣል። የኩላሊት ህመም ባለሙያው በዚህ መረጃ ውጤታማ የሕክምና ስትራቴጂ ማቀድ እና ህመምተኞችን እና ቤተሰቦቻቸውን በማሳተፍ ስለህመሙ ክብደት እና ሂደት በመከተል መምራት ይችላል።

የኩላሊት ባዮፕሲ በየትኛው ቴክኒክ ይከናወናል?

በጣም የተለመደው ዘዴ ፐርኪታንየስ ኒድል ባዮፕሲ የሚባለው ነው (ብዙውን ጊዜ በራጅ ክፍል ውስጥ ይከናወናል)። በዚህ ውስጥ አንድ ባዶ መርፌ በቆዳ ውስጥ ወደ ኩላሊት ይተላለፋል። ሌላው ብዙም ጥቅም ላይ የማይውል ዘዴ የቀዶ ጥገና ሥራን የሚፈልግ ክፍት ባዮፕሲ ነው (በቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ ይከናወናል)

የኩላሊት ባዮፕሲ ከመከወኑ በፊት የቅድመ ዝግጅቱ ሂደት ምንን ያካትታል?

  • ታካሚው ሆስፒታል ውስጥ ገብቶ ይሄንን ምርመራ እንዲደረግለት ፍቃደኛ መሆኑ ይመዘገባል።
  • ባዮፕሲ ከመደረጉ በፊት የደም ግፊት እና የደም መርጋት ላይ ችግር መኖር አለመኖሩ ያረጋግጣል።
  • የደም መርጋት (ለምሳሌ አስፕሪን እና ክሎፒድሮግል) ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚዉሉ መድኃኒቶች ባዮፕሲ ከመደረጉ አስቀድሞ፤ ቢያንስ ከ 1 እሰከ 2 ሳምንታት እንዲቋረጥ ይመከራል።
  • የአልትራሳውንድ ወይም ሲቲ ስካን ምርመራ የኩላሊቶችን አቀማመጥ ለማወቅ እና ትክክለኛውን የባዮፕሲ ጣቢያ ለማወቅ ይደረጋል።
  • ታካሚው በሆዱ እንዲተኛ ይጠየቃል። ሆዱም በትራስ ወይም በፎጣ ይደ ገፋል።
  • በልጆች ላይ፤ የኩላሊት ባዮፕሲ በአጠቃላይ ማደንዘዣ በመታገዝ ይከና ወናል ስለሆነም ህፃኑ ንቁ ሆኖ ሕመሙን አያዳመጥም።
  • ቆዳ በትክክል ካጸዳ በኋላ መርፌ በሚገባበት ቦታ ህመምን ለመቀነስ በአካባቢው ማደንዘዣ ይሰጠዋል።
  • ባዶ የባዮፕሲ መርፌን በመጠቀም እንደ ቁርጥራጭ 2 ወይም 3 ትናንሽ ክር መሳይ ቁርጥራጮች ከኩላሊት ይወሰዳሉ።
  • ከዚያም እነዚህ ዉጤቶች፤ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ላብራቶሪ ይላካሉ።
  • ከባዮፕሲው መከወን በኋላ የደም መፍሰስን ለመከላከል ባዮፕሲው ቦታ ላይ በእጅ ግፊት ይደረጋል። ታካሚው ለ 6-12 ሰዓታት ሳይንቀሳቀስ የአልጋ ላይ ዕረፍት የሚያደርግ ሲሆን፤ ብዙውን ጊዜ በሚቀጥለው ቀን ከሆስፒታል መውጣት ይፈቀድለታል።
  • ባዮፕሲው ከተደረገ በኋላ፤ ታካሚው ከባድ ሥራን ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ቢያንስ 2-4 ሳምንታት እንዲያቆም ይመከራል።

በኩላሊት ባዮፕሲ ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉ ያልታሰቡ አደጋዎች ይኖሩ ይሆን?

ልክ እንደ ማንኛውም የቀዶ ጥገና አሰራር ከኩላሊት ባዮፕሲ በኋላ በጥቂት ታካሚዎች ላይ አንዳንድ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ። በቀዳዳው ቦታ ላይ ቀላል ህመም እና ቀላ ያለ ሽንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ማየት የተለመደ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ግን ይህ ክስተት በራሱ ይቆማል።

የደም መፍሰስ በሚቀጥልባቸው ሁኔታዎች ግን፤ አልፎ አልፎ ደም መውሰድ ሊያስፈልግ ይችላል። በጣም አልፎ አልፎ በሚፈጠሩ ሁኔታዎች፤ ከባድ የደም መፍሰስ ከቀጠለ ግን ድንገተኛ ቀዶ ጥገናን በማድረግ ኩላሊትን ማስወገድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።

አልፎ አልፎ የተገኘው የኩላሊት ናሙና ለምርመራ በቂ ላይሆን ይችላል (20 ሰው ውስጥ 1 ሰው ላይ የሚከሰት አጋጣሚ አለ። በእዚህ ጊዜ ባዮፕሲውን መድገም ሊያስፈልግ ይችላል።