Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

18. የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን

የሽንት ማስተላለፊያ አካላት የምንላቸው ሁለት ኩላሊቶች ፣ ሁለት ሽንት ማሳለፊያ ቱቦዎች (ዩሬተር)፣ አንድ የሽንት ፊኛ እና የሽንት ቧንቧን (ዩሬትራ) ያካትታል።

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክቶች እንደ አምጪ ተህዋሲያኑ ፣ በዕድሜና ኢንፌክሽኑ የተከሰተበት ቦታ ይለያያሉ። ሆኖም በአብዛኛው የሚስተዋሉት

  • በሽንት ጊዜ ማቃጠልና የህመም ስሜት መኖር፤
  • ቶሎ ቶሎ መሽናትና አጣዳፊ የሆነ የመሸናት ፍላጎት መጣሁ መጣሁ ማለት፤
  • ትኩሳትና መቾት አልባነት ስሜት መኖር፤
  • መጥፎ የሽንት ጠረን እና ጉም መሰል ቀለም ሆኖ መታየት ይገኙበታል።

የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን ምልክቶች፡-

  • ከእምብርት በታች ያለመመቸት ስሜት
  • ቶሎ ቶሎ የሚመጣ ህመም ያለዉ መጠኑ ያነሰ ሽንት
  • 38 ዲግሪ ሴሊየስ በታች የሆነ ትኩሳት እና መራቢያ አካል አካባቢ ያለ ህመም
  • ደም የቀላቀለ ሽንት

በላይኛው የሽንት ማስተላለፊያ አካላት ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን (ፓይሎኔፍራይትስ) ምልክቶች፡-

  • የጀርባና የመራቢያ አካባቢ ህመም
  • ከፍተኛ ትኩሳትና ብርድ ብርድ የማለት ስሜት
  • ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ የድካም ስሜት መሰማት፣ አቅም ማነስ፣ ምቾት አልባነት፤
  • የአዕምሮ ሁኔታ መዘበራረቅና ግራ መጋባት የመጋባት ስሜት መኖር

እነዚህ ምልክቶች በሙሉ ሰውነት ላይ ተፅዕኖ እያመጣ ያለና ምናልባትም የተሰራጨ ኢንፌክሽን ስለሚያመላክቱ ከሌሎች የተለየ አትኩሮት ሊደረግባቸዉ ይገባል። ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቀርቶ፤ ተገቢውን ህክምና በተገቢው ወቅት ማድረስ ካልተቻለ ህይወት አደጋ ላይ ይወድቃል።

በተደጋጋሚ የሚያጋጥም የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምክንያቶቹ ምንድን ናቸው?

  1. የሽንት ቧንቧ መደፈን ወይም መጥበብ
  2. በፆታ ሴት መሆን:- የሴቶች የታችኛው የሽንት ቧንቧ (ዩሬትራ) አጭር በመሆኑ ኢንፌክሽን አምጪ ተህዋሲያን ወደላይ ለመውጣት ይቀላቸዋል።
  3. ፆታዊ ግንኙነት ያላቸዉ ሰዎች፤
  4. የሽንት ቧንቧ ጠጠር: በኩላሊት፣ በላይኛው የሽንት ቧንቧ (ዩሬተር) እና በፊኛ ውስጥ ያሉ ጠጠሮች ሽንት እንደልብ እንዳይወገድ በማድረግ ኢንፌክሽን እንዲፈጠር አስተዋፅኦ ያደርጋሉ።
  5. ካቲተር (የሽንት ማስወገጃ ቱቦ) መጠቀም፤
  6. ከውልደት ጀምሮ ያሉ የሽንት ቧንቧ እክሎች፤
  7. የፕሮስቴት ዕጢ፤
  8. የተዳከመ ህመምን የመከላከል አቅም መታየት
  9. ሌሎች ምክንያቶች፡- እንደ የሽንት እና መራቢያ አካላት ቲቢ፣ ፊኛ ሲሞላ አለመሰማት (ኒውሮጄኒክ የሽንት ፊኛ) ፣ የተከፈለ የሽንት ፊኛ (ብላደር ዳይቨርቲኩለም)

በተደጋጋሚ የሚያጋጥም የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ኩላሊትን ሊጎዳ ይችላል?

በሽንት ፊኛ እና በታቸኛው የሽንት ቧንቧ የሚያጋጥም ኢንፌክሽን አብዛኛውን ጊዜ በአዋቂዎች ላይ ለሚከሰት የኩላሊት ህመም የጎላ አስተዋፅዖ የለውም። ሆኖም እንደ ጠጠር፣ የሽንት ማስወገጃ ቱቦዎች መጥበብና መዘጋት እንዲሁም የሽንት ቧንቧ ቲቢ በጊዜው ካልታከመና ካልተስተካከሉ የኩላሊት ህመም ተጋላጭነትን ከሚጨምሩ ሁኔታዎች ዉስጥ ይመደባሉ።

በአንፃሩ ተገቢውን ህክምና ያለገኘን ፤ የታችኛውም ሆነ የላይኛው የሽንት ቧንቧ ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን እድገታቸውን ያልጨረሱ የህጻናት ኩላሊቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ህፃናት ላይ የሚከሰት የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሽንት አስተላላፊ አካላት ላይ ከሚኖሩ አካላዊ ችግሮች ማለትም ከፊኛ ወደ ላይኛው የሽንት ቧንቧ ሽንት የመመለስ ችግር እና የመሣሠሉትን ሊያመላክት ይችላል። እንደዚህ አይነት አካላዊ እክሎች ሳይስተካከሉ ከሰነባበቱ ወደኋላ ላይ የኩላሊት ስራ መዳከም ብሎም ከፍተኛ የደም ግፊት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ስለዚህም የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ከአዋቂ ይልቅ ህጻናት ላይ ከፍ ያለ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

ሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምርመራ

1. የሽንት ምርመራ: በጠዋት የሚወሰድ የሽንት ናሙና ተመራጭ ነው። ይህ ናሙና በማይክሮስኮፕ ሲታይ ነጭ የደም ሴሎች ከተገኙ የኢንፌክሽን መኖርን ቢያመላክትም ኣለመኖራቸው ግን ኢንፌክሽን አለመኖሩን አያረጋግጥም።

በቤት ውስጥ እና በሀኪሙ ቢሮ ሊሰሩ ከሚችሉ ቀላል ምርመራዎች መካከል አንዱ ዲፕስቲክ ነዉ። ይህ መሳሪያ ኢንፌክሽን መኖሩን የሚያሳየው የቀለም ለውጥ በማምጣት ሲሆን ቀለሙ ደመቅ ያለ ከሆነ ቁጥር በዛ ያሉ ባክቴሪያዎች መኖራቸውን ያሳያል። ሆኖም ብቻውን በቂ ምርመራ ስለልሆነ ሌሎች ምርመራዎች እንዲደረጉ ይመከራል።

2. ከሁሉም ምርመራዎች የላቀ ተብሎ የሚታሰበው በሽንት ውስጥ ያሉ ባክቴሪያዎችን በላቦራቶሪ የማሳደግ ምርመራ ነው። ይህንን ምርመራ የምንጠቀመው ታካሚው የተሰጡት መድሀኒቶች ሊያሽሉት ካልቻሉ ወይም በተደጋጋሚ በኢንፌክሽን የሚጠቃ ከሆነ የሞንሰጠውን መድሀኒት ለይቶ ለማወቅ እንዲረዳ ነው። ነገር ግን ውጤቱ ከ 48-72 ሰዓታት ሊፈጅ ይችላል።በዚህ ምርመራ የምናውቃቸው ዉጤቶች:- ኢንፊክሽኑን ያስከተለው የባክቴሪያ አይነት እና በየትኛው መድሀኒት መታከም እንደሚችል ናቸው።

ከሽንት ውጪ የሚመጡ ተህዋሲያን የምርመራውን ውጤት እንዳያዛቡብን ለማድረግ እንዲቻል፤ ናሙና ከመውሰድ በፊት ታካሚው በቅድሚያ የመራቢያ አካላታቸውን እና አካባቢውን በሚገባ ካፀዱ በኋላ ሽንት መሽናት ከጀመሩ ከጥቂት ሴኮንዶች በኋላ ናሙና የሚወስድ ይሆናል። በካቲተር የታገዘ ናሙና መውስድ እንደ አማራጭ ሊወሰድ ይችላል።

3. የደም ምርመራ: ሲቢሲ (ሙሉ የደም ሴል ቆጠራ)፣ የኩላሊት ምርመራ (የድም ክርያትኒን እና ዩርያ ፣ የስኳር ምረመራ እና ሲ ሪአክቲቭ ፕሮቲን ተደጋጋሚ ኢንፌክሽን ሲኖር እና በመድሀኒት መሻሻል ካልታየ ተጋላጭነትን የሚያሳዩ ሌሎች ምርመራዎች ሊደረጉ ይችላል። ከነዚህም ውስጥ

  1. አልትራሳውንድ እና የሆድ ራጅ
  2. ሲቲ ስካንና ኤም አር አይ
  3. በሽንት ጊዜ የሚደረግ ሲስቶ ዩሬትሮግሪም
  4. ኢንትራ ቬነስ ዩሮግራፊ
  5. የቲቢ ምርመራ
  6. ሲስቶስኮፕ: የሽንት ፊኛን ለማየት የሚደረግ ምርመራ
  7. የማህፀን ስፔሻሊስት ማማከር
  8. የሽንት ፍሰት ምርመራዎች
  9. በላቦራቶሪ በደም ውስጥ የሚገኙ ህዋሳትን ማሳደግ

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን መከላከል

መከላከያ መንገዶች

  1. ብዙ ውሃ መጠጣት (3-4 ሊትር)
  2. ሽንት በመጣ ጊዜ ወጥሮ ሳያቆዩ መሽናት
  3. ቫይታሚን ያላቸው ምግቦችን መመገብ
  4. ድርቀትን ሊያስከትሉ ከሚችሉ ምግቦች መራቅ ግድ ይሆናል፤
  5. ሴቶች ሲጸዳዱ ከፊት ወደ ኃላ መሆን አለበት
  6. መራቢያ አካላትንና አካባቢውን ከግብረ ስጋ ግንኙነት በፊትና በኋላ በሚገባ ማፅዳት። ከግንኙነት በፊትና በኋላ መሽናትና ውሃ መጠጣት
  7. ከጥጥ የተሰራ ዉስጥ ሱሪ መጠቀም፣ ከናይሎን የሚሰራና የሚያጠብቅ የዉስጥ ሱሬ አለመጠቀም፤
  8. ከግብረ ስጋ ግንኙነት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የሽንት ቧንቧ ኢንፊክሽን በአግባቡ በመድሀኒት ከታከመ ሊድን ይችላል።

ለመሆኑ እንዴት ይታከማል?

ዉሃ አብዝቶ መጠጣት እንደቀላል ሊታይ አይገባም። በጣም የታመመ ፣ የተጠማና ለመጠጣት የሚቸግረው ሰው ሆስፒታል ገብቶ በደም ስር ፈሳሾች ሊሰጡት ይገባል።

ትኩሳትና ህመም ካለ የሚያስታግሱ መድሀኒቶችን መውሰድ ይገባል። ከቡና ፣ አልኮል መጠጥ፣ ማጨስና የሚያቃጥል ምግብ መቆጠብ ፊኛ ላይ የሚደርስ መቆጣትን ይቀንሳል።

የታችኛው የሽንት ማስተላለፊያ አካላት ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን ሕክምና(የሽንት ቧንቧ ከረጢት)

የታችኛው የሽንት ማስተላለፊያ አካላት ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን እድሜያቸው ባልገፋ ሴቶች ላይ ሲከሰት እስከ ሶስት ቀን መድሀኒቶችን መውሰድ በቂ ነው። አንዳንድ መድሀኒቶች 7 ቀናት ሊሰጡ ይችላል። አንድ ጊዜ ብቻ የሚወሰድ ፎስፎማይሲን የተባለ መድሀኒት አለ። ወንዶች ከዚህ በፊት ጤነኛ ካልነበሩ በስተቀር የሽንት ማስተላለፊያ አካላት ችግር አለ ተብሎ ስለሚታመን ከ 7-14 ቀናት የሚወሰድ መድሀኒት ይስጣቸዋል። ናይትሮፉራንቶይን፣ ትራይሜቶፕሪም፣ ሴፋሎስፖሪን ወይም ፍሎሮኩዋኖሎን መጠቀም የሚቻል ሲሆን የቱን የሚለው በአካባቢውላይ ያለው የተህዋሲያን ለመድሀኒት ያላቸው መቋቋም ላይ ይወሰናል።

ከፍተኛ የኩላሊት ኢንፌክሽን (ፓይሎኔፍራይትስ) ሕክምና

ከፍተኛ የኩላሊት ኢንፌክሽን (ፓይሎኔፍራይትስ) በአብዛኛው በሆስፒታል ተኝተው መታከም ይኖርበቸዋል። መድሀኒት ከመጀመር በፊት የደምና የሽንት ተህዋሲያን በላቦራቶሪ ማሳደግ ተገቢ ነው፡ ታካሚው ሆስፒታል ከገቡ በኋላ በደም ስር የሚሰጡ ፈሳሾች እና የኢንፊክሽን መድሀኒቶች ለቀናት ከተሰጡ በኋላ የሚዋጡ የኢንፊክሽን መድሀኒቶት ከ10-14 ቀናት ይሰጣሉ። በደም ስር ለሚሰጡ መድሀኒቶች መሻሻል ካላሳዩ ማለትም ትኩሳት ካለና የኩላሊት ስራ መባባስ ካለ አልትራሳውንድ ራጅ ወይም ሲቲ ስካን ሊያስፈልግ ይችላል። ከዛም መድሀኒቶች መስራታቸውን ለማረጋገጥ በሽንት የሚሰሩ ምርመራዎች ሊታዘዙ ይችላል።

በተደጋጋሚ የሚከሰት ኢንፌክሽን ተጓዳኝ ችግሮች ካሉ እነርሡን ማረጋገጥና ከዉጤቱ በመነሳትም፤ መድሀኒት እና የቀዶ ጥገና ህክምና ላይ ይወሰናል። እነዚህ ታካሚዎች ክትትል እና መከላከያ መንገዶችንበተገቢ ሁኔታ እንደሚከተሉ ማረጋገጥ እና የረጅም ጊዜ መከላከያ መድሃኒቶች ያስፈልጓቸዋል።

መቼ ወደ ሀኪም ዘንድ መሄድ አለብዎ?

ህጻናት ሁሌም ሀኪም ዘንድ መቅረብ አላባቸው። አዋቂዎች የሽንት መጠን መቀነስ፣ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት የወገብ ህመም እና የሽንት ቀለም መቀየርና ደም መቀላቀል ፣ መድሀኒት እየወሰዱ ከ2 እስከ 3 ቀናት በኋላ አለመሻል፣ ማስመለስ፣ ድካም ስሜት እና የደም ግፊት መቀነስ፣ አንድ ኩላሊት ብቻ መኖር እና ጠጠር ከነበረ ወዲያውኑ ሀኪምዎ ዘንድ መቅረብ ያስፈልጋል።