Read Online in Amharic
Table of Content
መግቢያ እና ይዘቶች
መሰረታዊ መረጃ
የኩላሊት መድከም
ሌሎች ዋና ዋና የኩላሊት ህመሞች
የኩላሊት ህመም ወቅት አመጋገብ

7. የኩላሊት ህመም መከላከያዎች

የኩላሊት ህመሞች በአብዛኛዉ ምንም ምልክት አያሳዩም። የኩላሊት ህመሞች እየተባባሰ የሚሄድ የኩላሊት የሥራ አቅም ማነስ በማምጣት የኩላሊት መድከም ሊያስከትሉ ይችላሉ ህመሞቹ ደረጃቸዉ እያደገ ሲመጣም፤ ህይወትን ለማቆየት የኩላሊት እጥበት አልያም ንቅለ ተከላ ግድ እነዲሆን ያደረጋል። ባላደጉት ሀገራት ባለው ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ እና የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት እጥረት ምክንያት እድለኛ የሆኑት ማለትም፤ 5 እስከ 10 በመቶ የሚሆኑት ታማሚዎች ብቻ ናቸው ወሳኝ ህክምና የሆኑትን እንደ የኩላሊት እጥበት እና ንቅለ ተከላ አገልግሎት የሚያገኙት፤ የተቀሩት ደግሞ ወሳኝ ህክምና ባለማግኘታቸው ለሞት የሚዳረጉ ይሆናል። ስር ሰደድ የኩላሊት ህመም በጣም የተለመደ እና ፈዉስ አልባ ህመም ሲሆን ቀድሞ መከላከል ብ ቸኛው አማራጭ ነው። በጊዜ ህመሙ እንዳለብን ማወቁ እና ህክምና ማግኘቱ ህመሙ እንዳይባባስ እንዲሁም ዉድ እና ዉስብስብ የሆነ ህክምና ግድ እንዳይል አልያም ቢያስፈልግ እንኳን ጊዜዉን ለማራዘም ይረዳል።

የኩላሊት ህመም እንዴት እንከላከለዋለን?

ኩላሊቶቻችን ፈፅሞ ችላ ማለት የለብንም። አስፈላጊ እና ዋና ዋና ኩላሊትን ከህመሙ መጠበቂያ እና መከላከያ የመባሉ መንገዶችን ከዚህ በታች በሚገኙ ክፍሎች እንመለከታለን፡

  1. ጥንቃቄ ለጤናማ ሰው
  2. ጥንቃቄ ለኩላሊት ታማሚዎች

ጥንቃቄ ለጤናማ ሰው

ሰባት ውጤታማ የኩላሊት ጤና የምንጠብቅባቸዉ መፍትሄዎች

1. ንቁ እና ቀልጣፋ መሆን

መደበኛ ኤሮቢክ ስፖርት እና የዘወትር የአካል እንቅስቃሴ ጤናማ የሆነ የደም ግፊት መጠን እና የስኳር መጠናችንን እንድንቆጣጠር ይረዳል። እንዲህ አይነት የአካል እንቅስቃሴዎች የስኳር እና የከፍተኛ የደም ግፊት ህመም ተጋላጭነትን በመቀነስ የስር ሰደድ የኩላሊት ህመም ተጋላጭነትንም ይቀንሳል።

2. የተመጣጠነ ምግብ

ጤናማ አመጋገብ አትክልት እና ፍራፍሬ መመገብ። ፋብሪካ ውስጥ የተዘጋጁ ፣ ከፍተኛ ካሎሪ ያለባቸው ቅባት የበዛባቸው ምግቦች ስኳር ስጋና ቅባት ያላቸው ምግቦችን መቀነስ። ከ40 ዓመት በላይ ዕድሜ በሆኑት ዘንድ፤ የጨው መጠንን መቀነስ የኩላሊት ጠጠር እና የከፍተኛ የደም ግፊት ህመሙን ለመከላከል ይረዳል።

3. የሰውነት ክብደትን መቆጣጠር

የሰውነት ክብደታችንን ጤናማ በሆነ አመጋገብ እና በመደበኛ የስፖርት እንቅስቃሴ መቆጣጠር። ይህም እንደ ስኳር፣ የልብ ህመሙ እና የስር ሰደድ የኩላሊት ህመም ጋር ተያያThነት ያላቸው ችግሮች ተጋላጭነትን ይቀንሳል።

4. ሲጋራ ማጨስ እና የትንባሆ ውጤቶችን ማቆም

ማጤስ ለደም ቧምቧ ጥበት ያጋልጣል ይህም ደግሞ ወደ ኩላሊት የሚሄደው የደም መጠንን ይቀንሳል ፤በዚህም የተነሳ ኩላሊት ስራዉን በትክክል እንዳይሰራ ያደርጋል። የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱትም ትምባሆ ማጤስ በተለይ ኩላሊት ህመም ያለባቸው ሰዎች ላይ የኩላሊት የመስራት አቅም መዳከምን እንዲፋጠን ያደርጋል።

5. ከማዘዣ ዉጪ የሚሸጡ መድሃኒቶች መጠበቅ

ከማዘዣ ዉጭ የሚሽጡ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ከመጠን በላይ በተደጋጋሚ መጠቀም የለብንም። የተለመዱ መድሃኒቶች እንደ አይቡፕሮፌን እና ናፕሮዜን በተደጋጋሚ ከመጠን በላይ ከተወሰዱ ኩላሊት ላይ ጉዳት በማድረስ መድከምን እንደሚያምጡ ይታወቃል። ስለዚህ የህመም ስሜትን ለመቆጣጠር እና ለመቀነስ የተሻሉ ሌሎች አማራጮችን እንዲመክሮት ብሎም ኩላሊትዎን ለአደጋ በማያጋልጥ መልኩ መሆኑን ሃኪምዎትን ማማከር ይጠበቅቦታል።

6. በዛ ያለ ዉሀ መጠጣት

በቂ የሆነ ዉሀ መጠጣት (በቀን እስከ 3 ሊትር) ሽንትን ለማቅጠን፣ ከአካላችን የሚወጡ ቆሻሻ ነገሮችን ለማስወገድ እና የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል ይረዳል።

7. ዓመታዊ የኩላሊት ምርመራ ማድረግ

የኩላሊት ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ ዝምተኛ ስለሆነ፤ ከፍተኛ የሆነ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ ምንም አይነት ምልክት አያሳይም። በጣም ዉጤታማ የሆነው ነገር ግን እምብዛም ቦታ የማንሰጠዉ በጊዜ የኩላሊት ህመሙን ለማወቅ እና ለመከላከል የሚረዳው መደበኛ የሆነ በየጊዜው የሚደረግ የኩላሊት ምርመራ ነው። ከፍተኛ የሆነ ተጋላጭነት ያላቸው የስኳር፣ የከፍተኛ የደም ግፊት ህመም፣ ከመጠን በላይ ዉፍረት እና የቤተሰብ የኩላሊት በሽታ ታሪክ ያላቸው ሰዎች ዓመታዊ የሆነ የኩላሊት ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ኩላሊታችሁን የምትወዱ ከሆነ (ከምንም በላይ ደግሞ ራሳችን) 40 አመት እድሜ ከሞላዎት በኋላ መደበኛ የሆነ የኩላሊት ምርመራ ማድረግዎን አይርሱ። የኩላሊት ህመሙን በጊዜው ለማወቅ በትንሹ ዓመታዊ የሆነ የደም ግፊት ምርመራ፣ የሽንት ምርመራ እና የደም ዉስጥ የክሪያቲኒን መለካት ያስፈልጋል።

ጥንቃቄ ለኩላሊት ህመም ታካሚዎች

1. ስለኩላሊት ህመም ግንዛቤ እና በጊዜ ምርመራ ማድረግ

ንቁ ሆነን የኩላሊት ህመም ምልክቶች መከታተል። የተለመዱ የኩላሊት ህመም ምልክቶች የምንላቸው የእግርና የፊት ማበጥ፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ፣ የድካም ስሜት፣ ሽንት ቶሎ ቶሎ መሸናት፣ በሽንት ውስጥ የደም ወይም የፕሮቲን መገኘት ናቸው። እንደዚህ አይነት ምልክቶች ሲያጋጥሙን ሀኪም ማማከር አልያም የኩላሊት ምርመራ ማድረግ ይመከራል።

2. የስኳር ታማሚ በሆኑ የሚደረግ ጥንቃቄ

ለሁሉም የስኳር ታማሚዎች የኩላሊት ህመምን መከላከል በጣም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም የስኳር ህመም በአለም ላይ የስር ሰደድ የኩላሊት ህመም እና የኩላሊት መድከም ከሚያስከትሉ ህመሞች ዋነኛው እና ቀዳሚው ነው። 45% የሚሆኑ አዳዲስ የሆነ የመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም በስኳር ህመም የሚከሰት የኩላሊት ህመም ነው። በቀላሉ መንገድ በስኳር ህመም የሚመጣ የኩላሊት ህመምን ለመመርመር ቀላል እና ዉጤታማ የሆነው ዘዴ ቢያንስ በየወር አንዴ የሚደረግ የደም ግፊት ምርመራ እና በዲፕስቲክ በሽንት ውስጥ ያለውን የፕሮቲን መጠን ወይም ማይክሮ አልቢሚኑሪያ በሽንት ምርመራ ማጣራት ነው። ይህ በየዓመቱ መደረግ ያለበት በቶሎ በስኳር ህመም የሚመጣ የኩላሊት ህመምን ለመመርመር የሚረዳ የተሻለ እና አይነተኛ የሆነ ምርመራ ነው። ቢያንስ በየዓመቱ የኩላሊት የስራ አቅምን ለማወቅ የደም ውስጥ የክሪያቲኒን መጠን መለካት ያስፈልጋል።

ከፍተኛ የደም ግፊት፣ በሽንት ውስጥ የፕሮቲን መኖር፣ አጠቃላይ የሰውነት ማበጥ፣ በየጊዜው የሚለዋወጥ የስኳር መጠን፣ የኢንሱሊን አስፈላጊነት መቀነስ እና በስኳር ህመም የሚመጣ የአይን ህመም ምኖር ስኳር ያለባቸው ሰዎች ኩላሊታቸው መጎዳቷን የሚያመለክቱ ናቸው። ከነዚህን የአደጋ ምልክቶች መጠንቀቅ እና ሀኪምን ወዲያው ማማከር አለብን።

በስኳር ህመም የሚከሰቱ የኩላሊት ህመምን ለመከላከል አንድ የስኳር ህመምተኛ የስኳር መጠኑን በሚገባ መቆጣጠር፣ የደም ግፊት መጠን ከ 130 በ 80 ሚሊ ሜርኩሪ በታች እንዲሆን መቂጣጠር፣ የፕሮቲን ያላቸው ምግቦች መቀነስ እና የስብ መጠንን መቆጣጠር አለበን።

3. ከፍተኛ የደም ግፊት ታማሚዎች የሚደረግ ጥንቃቄ

ከፍተኛ የደም ግፊት የስር ሰደድ የኩላሊት ህመምን ከሚያስከትሉ የተለመዱ ምክንያቶች ሁለተኛው ነው። አብዛኛዎቹ የከፍተኛ የደም ግፊት ታማሚዎች ምንም አይነት ምልክት አያሳዩም፣ አብዛኛዎቹ ታማሚዎች የታዘዙላቸውን መድሃኒቶች በአግባቡ አይወስዱም፣ አንዳንዶች ደግሞ የህክምና ክትትላቸውን ሙሉ ለሙሉ እሰከማቋረጥ ይደርሳሉ። መድሃኒት አለመውሰድ ስለሚመርጡ ህክምናዉን ያቋርጣሉ ይህ እጅግ በጣም አደገኛ ነው። ለረጅም ጊዜ ከቁጥጥር ዉጪ የሆነ የከፍተኛ የደም ግፊት ከፍተኛ ችግር ለሆነ እንዳለ ስር ሰደድ የኩላሊት ህመም፣ ለልብ ድካም እና ለስትሮክ አልያም በደም መመታት ያጋልጣሉ።

የኩላሊት ህመሙን ለመከላከል ሁሉም የከፍተኛ የደም ግፊት ታማሚዎች የታዘዘላቸውን የደም ግፊት መድሀኒት በትክክል መውሰድ፣ በጊዜው የደም ግፊት መጠናቸዉን መለካት እና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እና የጨው መጠንን መቀነስ ያስፈልጋል። የህክምናው ዋናው ዓላማ የደም ግፊት መጠንን 130/80 ሚሊ ሜርኩሪ እና ከዛ በታች ማድረግ ነው። በጊዜ የኩላሊት መጎዳትን ለመመርመር ሁሉም ከፍተኛ የደም ግፊት ታማሚዎች የሽንት እና የደም ክሪያቲኒን መጠን በየዓመቱ መለካት አለባቸው።

4. የስር ሰደድ የኩላሊት ህመም ታማሚ በሆኑ የሚደረግ ጥንቃቄ

የስር ሰደድ የኩላሊት ህመም የማይድን ህመም ነው። ነገርኝ በቶሎ ተመርምሮ ከታወቀ እና የአመጋገብ ስርአታችንን ከተቆጣጠርን፤ መደበኛ የሆነ ክትትል እና ህክምና ካገኘን፤ እየተባባሰ መሄዱን በመቀነስ ወደፊት የኩላሊት አጠባ እና ንቅለ ተከላ በተሎ እንዳያስፈልግ ያደርጋል። ሁልጊዜ የደም ግፊት መጠንን መቆጣጠር የስር ሰደድ የኩላሊት በሽታ እንዳይባባስ ቁልፍ ሚና አለው። የደም ግፊት መጠንን 130/80 ሚሜ ሜርኩሪ እና ከዛ በታች ማድረግ እጅጉን ይመከራል። በጥሩ መልኩ የደም ግፊት መጠንን በቤት ውስጥ እየለኩ መመዝገብ ሀኪማችን መድሃኒቶችን እንዲያስተካክል ወይም እንዲለውጥ እጅግ በጣም ይረዳል።

ለስር ሰደድ ህመም ታማሚዎች የሚጎዱ እንደ ደም ግፊት መቀነስ፣ ድርቀት፣ የሽንት ቧንቧ በዘጋት፣ የደም መቆሸሽ፣ እና ኩላሊት የሚጎዳ መድሃኒቶች እና ወዘተ በፍጥነት መታወቅ አለባቸው። እነዚህ ችግሮች በፍጥነት ህክምና ማግኘት ጥሩ እና ጠንካራ የሆነ የኩላሊት አቅም እንዲኖር ያደርጋል። አንዳንዴም የኩላሊት አቅም እንዲሻሻል ያደርጋል።

5. የፖሊሲስቲክ የኩላሊት ህመም በጊዜ መመርመር እና ህክምና ማግኘት

አውቶሶማል ዶሚናንት ፖሊሲስቲክ የኩላሊት ህመም የተለመደ እና በጣም አስጊ የሆነ በዘር የሚተላለፍ የኩላሊት ህመም ሲሆን ከእስከ 8% ያክል ዲያሊሲስ የሚያደርጉ ታማሚዎች ጋር ይይዛል። የፖሊሲስቲክ የኩላሊት ህመም ታማሚ ቤተሰብ ያለው አንድ አዋቂ ከፍተኛ ተጋላጭነት ስላለው ህመሙ በጊዜ ካለበት እንዲታወቅ የአልትራሳውንድ ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል። የፖሊሲስቲክ የኩላሊት ህመም እንደ የከፍተኛ የደም ግፊትን በመቆጣጠር  የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽኖችን በማከም  አመጋገብን በመገደብ እና አጋTh ህክምናዎች ምልክቶችን ለመቆጣጠር እና ተጨማሪ ችግሮችን በመከላከል እና የኩላሊት የመድከም ፍጥነትን ከመቀነስ በስተቀር የማያዳግም ፈውስ የለውም።

6. የልጆች ሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ቅድመ ምርመራ እና ሕክምና

የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን አንድ ህፃን መነሻው ያልታወቀ ትኩሳት ፣ በተደጋጋሚ መሽናት  በሽንት አወጋገድ ወቅት የማቃጠልና የተለየ የህመም ስሜት መኖር  የምግብ ፍላጎት መቀነስ ወይም የክብደት ለዉጥ አለመኖር በሚከሰትበት ጊዜ ሁሉ መጠርጠር አለብን። እያንዳንዱ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንን ማስታወስ በጣም አስጊ ነው ፣ በተለይም ትኩሳት ያለው በኩላሊት ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል  በተለይ ዘግይቶ ከተመረመረ እና ተገቢ ባልሆነ ከታከመ። እንዲህ ዓይነቱ ጉዳት የኩላሊት ጠባሳ ፣ መጥፎ የሕፃናት ኩላሊት እድገት ፣ የደም ግፊት እና የኋላ ኋላ በህይወት ውስጥ የኩላሊት መድከም ያጠቃልላል። በዚህ ምክንያት  ተገቢው ህክምና ወዲያውኑ እንዲሰጥ በልጆች ላይ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ቶሎ መመርመሩ በጣም አስፈላጊ ነው ፣ በተጨማሪም አንድ ልጅ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሲይዘው ፣ የተጋለጡ ያልተለመዱ ነገሮችን ለይቶ ማወቅ ወይም ሌሎች ለአደጋ አጋላጭ ምክንያቶች መኖሩ በፍጥነት ማወቁ አስፈላጊ ነው። በልጅነት ጊዜ ወደ 50 በመቶ የሚሆነው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ውስጥ የቬዚኮዩሬትሪክ ሪፍልክስ በጣም የተለመደዉ አይነት አጋላጭ ሁኔታ ነው። በሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን በተጎዱ ሕፃናት ላይ የቅርብ ክትትል ማድረግ በተለየ መልኩ አስፈላጊ ነው።

7. ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን በጎልማሶች ላይ

ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ወይም ለተገቢው አንቲባዮቲክ ሕክምና በቂ ያልሆነ ምላሽ ያላቸው ታካሚዎች፤ ለዚህ አጋላጭ ምክንያቶች መገምገም አለባቸው። አንዳንድ መሰረታዊ ምክንያቶች (የሽንት ቧንቧ መዘጋት ፣ የጠጠር በሽታ ወዘተካልታከመ በኩላሊት ላይ ዘላቂ አደጋን ይከስታል። ስለሆነም የመነሻ ምክንያቶች ማወቅ እና መርመራ መሰረታዊ ጉዳይ ነው።

8. ትክክለኛ የፕሮስቴት ህመም

የፕሮስቴት ህመም ችግር ያለባቸው ብዙ ወንድ አዛውንቶች ምልክቶቻቸውን ለረጅም ጊዜ ችላ ይላሉ ምክንያቱም የመደበኛው የእርጅና ሂደት አካል በመሆናቸው የሽንት መሽናት ወይም የሽንት መንጠባጠብ የተለመደ ነው የሚለው የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው። ያልታከመ የፕሮስቴት ህመም በኩላሊት ላይም ዘላቂ ጉዳት ያስከትላል። ትክክለኛ ክትትል እና ወቅታዊ ህክምና በምርመራው ወቅት የቀረውን የኩላሊት ሥራ ተንከባክቦ ለማቆየት ይረዳል።

9. በወጣትነትዎ ጊዜ የደም ግፊትን ችላ አለማለት

በወጣትነት ጊዜ የደም ግፊት ያልተለመደ እና አብዛኛውን ጊዜ መንስኤውን ከስር መሰረት መመርመርን ይጠይቃል። በወጣቶች ላይ የኩላሊት ህመሞች ለፍተኛ የደም ግፊት ህመም ከተለመዱት መንስኤዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። ስለሆነም የደም ግፊት ያለባቸው ወጣቶች አፋጣኝ ግምገማ የኩላሊት ህመምን በጊዜ ለይቶ በማወቅ እና በመመርመር ዘላቂ ጉዳት የማድረስ ሂደትን ለመከላከል የግድ አስፈላጊ ነው።

10. አጣዳፊ የኩላሊት መድከም የመጀመሪያ ህክምና/ አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት

ለአጣዳፊ የኩላሊት መድከም ዋና መንስኤ የሚሆኑት (የኩላሊት ሥራን በድንገት መቀነስ) ተቅማጥ ፣ ማስታወክ ፣ የፋልሲፓረም ወባ ፣ የደም ግፊት መቀነስ ፣ የደም መቆሸሽ ፣ አንዳንድ መድኃኒቶች ናቸው። እነዚህን መነሻ ምክንያቶች በቅድሚያ እና በፍጥነት ለይቶ ማወቅ የቋሚ የኩላሊት መዳከምን እና መባባስን ይከላከላል።

11. ጥንቃቄ የተሞላበት የመድሃኒት አጠቃቀም

ንቁ ሁኑ- ብዙ ያለ ማዘዣ የሚሸጡ መድሃኒቶች (በተለይም የህመም ማስታገሻዎች እና የህመም ገዳይ) በተለይም በጎልማሶች/በትላልቆች ለኩላሊት ጉዳት አጋላጭ ነው። እንደነዚህ ዓይነቶቹ መድኃኒቶች በሰፊው ይተዋወቃሉ ፣ ግን አደገኛ ውጤቶቻቸው እምብዛም አይገለጹም። ለራስ ምታት እና ለአጠቃላይ የሰውነት ህመም የሚረዱ ያለ ማዘዣ የሚሸጡ የህመም ማስታገሻዎች (የህመም ገዳዮች) መጠቀምን ያስወግዱ። በራሳችን መድሃኒቶችን መውሰድ እና አላስፈላጊ መድሃኒቶችን ወይም የአመጋገብ ማሟያ መጠቀም ያስወግዱ። በሐኪም መመሪያ እና ቁጥጥር ስር የሚወሰዱ መድኃኒቶች ብዙውን ጊዜ አስተማማኝ ናቸው። ሁሉም የተፈጥሮ መድሃኒቶች (አዩርቪዲክ መድኃኒቶች ፣ የቻይናውያን ቅጠላ ቅጠል እና ስራ ስሮችእና የአመጋገብ ማሟያዎች ምንም ጉዳት የላቸውም የሚለውም እምነት የተሳሳተ ነው። በአዩርቪዲክ መድኃኒቶች ውስጥ ያሉ ከባድ ብረቶች በኩላሊቱ ላይ የማይቀለበስ ጉዳት እንደሚያደርሱ ታውቋል።

12. ጥንቃቄዎች በተናጥል ኩላሊት                                            

በአንድ ነጠላ ኩላሊት የሚኖር ሰው ጤናማ ኑሮ መኖር ይችላል። ሁለት ኩላሊት ያላቸው ታካሚዎች ሁሉ የደም ግፊቶቻቸውን ሁል ጊዜ መቆጣጠር፣ ብዙ ፈሳሾችን መውሰድ ፣ ጤናማ አመጋገብን መጠበቅ ፣ ከመጠን በላይ የጨው መጠንን መቀነስ ፣ ከፍተኛ የፕሮቲን ምግቦችን ማስወገድ እና ለብቸኛ ኩላሊት ጉዳት (ለምሳሌ ቀጥተኛ አደጋ) እንዳይደርስ መቆጠብ አለባቸው።በጣም አስፈላጊው ጥንቃቄ መደበኛ የሕክምና ክትትል ማድረግ ነው። አንድ ሰው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ የኩላሊት የስራ አቅምን ለመፈተሽ ሀኪምን በማማከር የደም ግፊትን ፣ የሽንት ምርመራን እና የደም ምርመራዎችን በማድረግ ፣ ከተፈለገም የመነሻውን የኩላሊት አልትራሳውንድግራፊን ማካሄድ ይኖርበታል።