ጠቅላላ እርምጃዎች
ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሁሉንም የመከላከያ እርምጃዎች መከተል አለባቸው
- የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ያለው ልጅ ብዙ ውሃ እንዲጠጣ ሊመክር ይገባል። የታመሙ እና በሃኪም ቤት እየቆዩ ላሉ ህጻናት በደምስር ፈሳሽ መስጠት ያስፈልጋል።
- ለትኩሳት ተገቢ መድሃኒቶች መሰጠት አለባቸው።
- ኢንፌክሽኑ በበቂ ሁኔታ እንደተቆጣጠረ ለማረጋገጥ የሽንት ካልቸር እና ሴንሴቲቪቲ ምርመራዎችን ህክምናው ከተጠናቀቀ በኋላ መደረግ አለባ ቸው። ኢንፌክሽን አለመኖሩን ለማረጋገጥ ለሁሉም ልጆች የሽንት ምርመ ራዎችን አዘውትሮ በመስራት መከታተል አስፈላጊ ነው።
ዋና ሕክምና
- የልጆችን በማደግ ላይ ያሉ ኩላሊቶችን ለመጠበቅ ሳይዘገይ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ወይም ዩቲአይ በአንቲባዮቲክ መታከም አለበት።
- ተህዋሲያን ባክቴሪያዎችን ለመለየት እና አንቲባዮቲኮችን በትክክል ለመ ምረጥ ህክምና ከመጀመራቸው በፊት የሽንት ካልቸር መሰራት አለበት።
- አንድ ልጅ በከፍተኛ ደረጃ ትኩሳት ፣ ማስታወክ ፣ ከባድ የጎን ህመም ካለበት እና በአፍ መድኃኒት መውሰድ ካልቻለ ሆስፒታል መተኛት እና የደም ሥር አንቲባዮቲኮችን መስጠት ያስፈልጋል።
- በአፍ የሚወሰዱ መድኃኒቶችን መውሰድ ለሚችሉ ከ 3 እስከ 6 ወር ዕድሜ ላላቸው ልጆች በአፍ የሚወሰድ አንቲባዮቲክ መድኃኒት ሊሰጥ ይችላል።
- ምንም እንኳን ህፃኑ የዩቲአይ ምልክቶች ባይኖሩትም እንኳ ልጆች የታዘ ዙትን አንቲባዮቲክ መድኃኒቶች ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቁ አስፈላጊ ነው።
ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ተደጋጋሚ ፣ ምልክት ያለው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ያለባቸው ልጆች ላይ ዋናውን ምክንያት ለመለየት እንደ አልትራሳውንድ ፣ ቪሲዩጂ እና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የዲኤምኤስኤ ስካን የመሳሰሉ ተጨማሪ ምርመራዎች ያስፈልጋሉ። ለተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የሚያመጡ ሶስት መታከም የሚችሉ ዋና ችግሮች ቬሲኮዩሬትራል ሪፍሌክስ ፣ ፖስቲርየር ዩሬትራል ቫልቭ እና የኩላሊት ጠጠር ናቸው። መሠረታዊውን መንስኤ መሠረት ተገቢው ሕክምና፣ የመከላከያ እርምጃዎች እና የረጅም ጊዜ የመከላከያ አንቲባዮቲክ ሕክምና ይታቀዳል። ለተወሰኑ ልጆች የቀዶ ጥገና ሕክምና በኔፍሮሎጂስት እና ዩሮሎጂስት በጋራ የሚታቀድ ይሆናል።
ፖስቴሪየር ዩሬትራል ቫልቭ
ፖስቴሪየር ዩሬትራል ቫልቭ በወንዶች ልጆች ላይ ከወሊድ ጀምሮ የሚከሰት የታችኛው የሽንት ቧንቧ ላይ የሚኖር ችግር ነው። በወንድ ልጆች ላይ ለሚከሰት የታችኛው የሽንት ቧንቧ መዘጋት የተለመደ ምክንያት ነው። መሰረታዊ ችግር እና አስፈላጊነቱ፡- ፒዩቪ በሽንት ቧንቧው ውስጥ ያሉት የቲሹ እጥፋቶች መደበኛ የሽንት ፍሰት በከፊል መቋረጥን ያስከትላል። በታችኛው የሽንት ቧንቧው ውስጥ የሽንት ፍሰት መዘጋት በሽንት ፊኛ ላይ ግፊት ይፈጥራል። የፊኛው መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል እና የጡንቻ ግድግዳው በጣም ወፍራም ይሆናል። ከፍ ያለ የፊኛ ግፊት ያለው ትልቅ የሽንት ፊኛ በላይኛው የሽንት ቧንቧ እና በኩላሊት ላይ ግፊት እንዲጨምር ያደርጋል። ይህ የሽንት ቧንቧዎችን እና የፐሊቪካልሴል (የማስወገጃ) ስርዓት መስፋትን ያስከትላል። እንዲህ ዓይነቱ መስፋት ፣በወቅቱ ካልተመረመረ እና ሕክምና ካልተደረገለት በረጅም ጊዜ ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ያስከትላል።
ከ 25% እስከ 30% የሚሆኑት ከፒዩቪ ጋር የተወለዱ ሕፃናት በመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም (ኢኤስኬዲ) ይሰቃያሉ። ስለዚህ ፒዩቪ በሕፃናት እና በልጆች ላይ ለበሽታ እና ለሞት መከሰት ከፍተኛ ምክንያት ነው። ምልክቶች:- ፖስቴሪየር ዩሬትራል ቫልቭ ላይ የተለመዱ ምልክቶች ደካማ የሽንት ፍሰት ፣ የሽንት መንጠባጠብ ፣ ለመሽናት መቸገር እና መጣር ፣ አልጋ ላይ መሽናት ፣ የተለጠጠ የሽንት ፊኛ እና በሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምክንያት የሆድ የታችኛው ክፍል መሙላት ናቸው።
ምርመራ፡- ከወሊድ በፊት (ቅድመ ወሊድ) ወይም ለወንድ ልጅ ከተወለደ በኋላ አልትራሳውንድ መስራት ለፒዩቪ ምርመራ የመጀመሪያ ፍንጭ ይሰጣል። የፒዩቪ ምርመራን ለማረጋገጥ ወዲያውኑ በድህረ-ወሊድ ጊዜ ውስጥ የቪሲዩጂ ምርመራ ያስፈልጋል። ሕክምና: የቀዶ ጥገና ሐኪሞች (ዩሮሎጂስቶች) እና የኩላሊት ስፔሻሊስቶች (ኔፍሮሎጂስቶች) በጋራ የፒዩቪን ሕክምና ያደርጋሉ። ለአስቸኳይ መሻሻል የመጀመሪያው ህክምና ሽንት ያለማቋረጥ ለማፍሰስ በሽንት ፊኛ (አብዛኛውን ጊዜ በሽንት ቧንቧ እና አልፎ አልፎ በቀጥታ በሆድ ግድግዳ በኩል አንድ ቱቦ ማስገባት ነው። እንደ ኢንፌክሽን ፣ የደም ማነስ እና የኩላሊት መድከምን ህክምና እንዲሁም የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን፣ የፈሳሽ እና የኤሌክትሮላይት እክሎችን ማስተካከል በተመሳሳይ ጊዜ የሚወሰዱ እርምጃዎች አጠቃላይ ሁኔታን ለማሻሻል ይረዳሉ። የፒዩቪ ትክክለኛ ህክምና ኢንዶስኮፕን በመጠቀም ቫልቩን በቀዶ ጥገና ማስወገድ ነው። ሁሉም ልጆች በኔፍሮሎጂስት መደበኛ የእድሜ ልክ ክትትል ያስፈልጋቸዋል ምክንያቱም የዩቲአይ፣ የእድገት ችግሮች ፣ የኤሌክትሮላይት መዛባት ፣ የደም ማነስ ፣ የደም ግፊት እና ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ የመከሰት እድል ስለሚኖር ነው።
ቬሲኮዩሬትራል ሪፍሌክስ (VUR)
ቬሲኮዩሬትራል ሪፍሌክስ “ከሽንት ፊኛ ወደ ላይኛው የሽንት ቧንቧ የኋላ የሽንት ፍሰት መኖር” ነው።
ስለ ቬሲኮዩሬትራል ሪፍሌክስ ማወቅ ለምን አስፈላገ?
ቪዩአር ከ 30 እስከ 40% ከትኩሳት ጋር በተዛመደ ዩቲአይ በሽታ ካለባቸው ሕፃናት ውስጥ ይገኛል። በብዙ ሕፃናት ላይ ቪዩአር የኩላሊት ጠባሳ እና ጉዳት ያስከትላል።
የኩላሊት ጠባሳ በረThም ጊዜ የደም ግፊት ፣ ወጣት ሴቶች ላይ የእርግዝና ህመም ፣ ሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም እና በጥቂት ታካሚዎች ውስጥ የመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት ህመም ያስከትላል። ቪዩአር ከቪዩአር ያለበት ሰው የቤተሰብ አባላት ላይ የበለጠ የተለመደ ሲሆን እንዲሁም በሴት ልጆች ላይ በተደጋጋሚ ይከሰታል።
የቬሲኮዩሬትራል ሪፍሌክስ (VUR) ምንድን ነው እና ለምን ይከሰታል?
ቪዩአር ከሽንት ፊኛ ወደ ላይኛው የሽንት ቧንቧ እና ምናልባትም እስከ ኩላሊት ድረስ ያልተለመደ የኋላ የሽንት ፍሰት ያለበት ሁኔታ ነው። ይህ በአንዱም ሆነ በሁለቱም ወገን ሊከሰት ይችላል።
በኩላሊት ውስጥ የተሠራው ሽንት በላይኛው የሽንት ቧንቧዎች በኩል ወደ የሽንት ፊኛ ይወርዳል። ሽንት በመደበኛነት በአንድ አቅጣጫ ፣ ወደ ላይኛው የሽንት ቧንቧዎች ከዛም ወደ የሽንት ፊኛ ይፈሳል። በሚሸናበት ጊዜ እና የሽንት ፊኛ በሽንት በሚሞላበት ጊዜ ፣ በሽንት ፊኛው እና በላይኛው የሽንት ቧንቧ መካከል ያለው ቫልቭ የኋላ የሽንት ፍሰት እንዳይከሰት የማድረግ ያደርጋል። ቪዩአር የሚከሰተው በዚህ ቫልቭ አሠራር ጉድለት ምክንያት ነው። ከሽንት ፊኛ እስከ የላይኛው የሽንት ቧንቧ እንዲሁም ኩላሊት ድረስ ያለው የኋላ የሽንት ፍሰት ክብደት ላይ በመመርኮዝ ቪዩአር ከቀላል እስከ ከባድ (ከ 1 እስከ 4 ደረጃ) ሊመደብ ይችላል።

የቬሲኮዩሬትራል ሪፍሌክስ መንስኤ ምንድነው?
ሁለት የ ቪዩአር ዓይነቶች አሉ-የመጀመሪያ ደረጃ ቪዩአር እና ሁለተኛ ደረጃ ቪዩአር ናቸው። የመጀመሪያ ደረጃ ቪዩአር በጣም የተለመደ የቪዩአር ዓይነት ሲሆን ከወሊድ ጊዜ ጀምሮ ይኖራል። ሁለተኛ ደረጃ ቪዩአር በማንኛውም ዕድሜ ላይ ሊከሰት ይችላል። ከሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን ጋር ተያይዞ ብዙውን ጊዜ በሽንት ፊኛ ወይም በታችኛው የሽንት ቧንቧ በመዘጋቱ ምክንያት ይከሰታል።
የቬሲኮዩሬትራል ሪፍሌክስ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
ለቪዩአር ምንም የተወሰኑ ምልክቶች የሉትም። ነገር ግን ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን (ዩቲአይ) በጣም የተለመደ የ ቪዩአር ምልክት ነው። በዕድሜ ከፍ ባሉ ልጆች ላይ ያልታከመ ከባድ ቬሲኮዩሬትራል ሪፍሌክስ እንደ የደም ግፊት ፣ በሽንት ውስጥ ከፍ ያለ ፕሮቲን መኖር ወይም የኩላሊት መዳከምን የመሳሰሉ ችግሮች መወሳሰብ ተከትሎ ምልክቶች ይታያሉ።
የቬሲኮዩሬትራል ሪፍሌክስ ምርመራ እንዴት ነው?
በቪዩአር የተጠረጠሩ ሕፃናት ላይ የሚደረጉ ምርመራዎች-
ለቪዩአር መሠረታዊ ምርመራ ቮይዲንግ ሲስቶዩሬትሮግራም - ቪሲዩጂ ለቬሲኮዩሬትራል ሪፍሌክስ ምርመራ እና ክብደቱን (ደረጃውን) ለማወቅ ወሳኝ ምርመራ ነው። ቬሲኮዩሬትራል ሪፍሌክስ እንደ የኋላ ፍሰቱ መጠን ደረጃ ተሰጥቶታል። የቪዩአር ደረጃ ምን ያህል ሽንት ከሽንት ፊኛ ወደ ላይኛው የሽንት ቧንቧ እና ኩላሊት ወደ ኋላ እየፈሰሰ መሆኑን ያሳያል። ደረጃ መሰጠቱ ለህመምተኛው ቅድመ-ትንበያ እና ተገቢውን ህክምና ለመወሰን አስፈላጊ ነው። መለስተኛ(ደረጃ 1 እና 2) በሆነ ቪዩአር የሽንት የኋላ ፍሰት ወደ ላይኛው የሽንት ቧንቧ ብቻ ነው። በጣም ከባድ በሆነ ቪዩአር ዉስጥ ከፍተኛ የኋላ የሽንት ፍሰት ጋር ተያይዞ የላይኛው የሽንት ቧንቧ መስፋት እና ከባድ የኩላሊት እብጠት (ደረጃ 5) ይኖራል።
በቪዩአር ውስጥ ተጨማሪ ምርመራዎች
- የሽንት ምርመራ እና የሽንት ካልቸር- የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንን ለመለየት ያገለግላል።
- የደም ምርመራዎች-ብዙውን ጊዜ የሚከናወኑ መሠረታዊ ምርመራዎች ሂሞግሎቢን ፣ ነጭ የደም ሴሎች መጠን እና የሴረም ክሬቲኒን ናቸው። የሴረም ክሬቲኒን የኩላሊትን ተግባር መለኪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።
- የኩላሊት እና የሽንት ፊኛ አልትራሳውንድ- የኩላሊቱን መጠን እና ቅርፅ ለማወቅ እና ጠባሳዎችን ፣ የኩላሊት ጠጠሮችን ፣ መሰናክልን ወይም ሌሎች ያልተለመዱ ነገሮችን ለመለየት ያስችላል። የኋላ ፍሰትንም ግን ለመለየት አይችልም።
- የዲኤምኤስኤ የኩላሊት ስካን- ይህ የኩላሊት ጠባሳዎችን ለመለየት በጣም የተሻለው ዘዴ ነው።
ቬሲኮዩሬትራል ሪፍሌክስ እንዴት ይታከማል?
ሊከሰቱ የሚችሉ ኢንፌክሽኖችን እና የኩላሊት መጎዳትን ለመከላከል ቪዩአርን ማከም አስፈላጊ ነው። የቬሲኮዩሬትራል ሪፍሌክስ ህክምና በየኋላ ፊሰቱ ደረጃ ፣ በልጆች ዕድሜ እና በምልክቶች ላይ የተመሠረተ ነው። ለቪዩአር ሦስት የሕክምና አማራጮች አሉ- አንቲባዮቲክስ ፣ የቀዶ ጥገና እና የኢንዶስኮፒ ሕክምና።
የቪዩአር በጣም የተለመደው የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና ዩቲአይንን ለመከላከል አንቲባዮቲክን መጠቀም ነው። የቀዶ ጥገና እና የኢንዶስኮፒ ሕክምና ለከባድ ቪዩአር ወይም አንቲባዮቲክ ውጤታማ ባልሆኑባቸው ሁኔታዎች ውስጥ የምንጠቀማቸው ናቸው። መለስተኛ ቪዩአር:- መለስተኛ ቪዩአር አንድ ልጅ ከ 5 እስከ 6 ዓመት በሆነው ጊዜ ሙሉ በሙሉ በራሱ ይጠፋል። መለስተኛ ቪዩአር ያላቸው ሕፃናት የቀዶ ጥገና ሕክምና የመፈለግ ዕድላቸው አነስተኛ ነው። በእንደዚህ ዓይነት ታካሚዎች ውስጥ ዝቅተኛ መጠን ያለው የአንቲባዮቲክ መጠን የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንን ለመከላከል ረዘም ላለ ጊዜ በቀን አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ይሰጣል። ይህ አንቲባዮቲክ ፕሮፊላክሲስ ይባላል። አንቲባዮቲክ ፕሮፊላክሲስ ብዙውን ጊዜ ታካሚው አምስት ዓመት እስኪሞላው ድረስ ይሰጣል። አንቲባዮቲኮች ቪዩአርን እንደማያስተካክሉ ማስታወስ ያስፈልጋል። ለአንቲባዮቲክ ፕሮፊላክሲስ ተመራጭ መድኃኒቶች ናቸው። የቪዩአር በሽታ ያላቸው ሁሉም ልጆች ለሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን አጠቃላይ የመከላከያ እርምጃዎችን (ከዚህ በላይ ተብራርቷል) መከተል እና በመደበኛነት፣ በተደጋጋሚ ሁለት ጊዜ መሽናት አለባቸው። የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንን ለመለየት በየጊዜው የሽንት ምርመራዎች ያስፈልጋሉ። የኋላ ፍሰት እንደቀነሰ ለመለየት ቪሲዩጂ እና አልትራሳውንድ በየአመቱ በድጋሜ ይመረመራሉ።
ከባድ ቪዩአር- ከባድ ቪዩአር በራሱ የመጥፋት እድሉ አነስተኛ ነው። ከባድ ቪዩአር ያላቸው ልጆች የቀዶ ጥገና ወይም የኢንዶስኮፒ ሕክምና ይፈልጋሉ።
የኋላፍሰትን በክፍት ቀዶ ጥገና ማረም የሽንት መመለስን ይከላከላል። የቀዶ ጥገናው ዋነኛው ጠቀሜታ ከፍተኛ የስኬት መጠኑ (88-99%) ነው። የኢንዶስኮፒ ሕክምና ለከባድ ቪዩአር በሽታ ሁለተኛ ውጤታማ የሕክምና ዘዴ ነው። የኢንዶስኮፒክ ቴክኒክ ጥቅሞች በተመላላሽ ታካሚ ደረጃ መከናወን መቻሉ ፣ 15 ደቂቃዎችን ብቻ መውሰዱ ፣ አነስተኛ አደጋዎች ያሉበት እና ምንም አይነት መቅደድ ወይም ቆዳ መክፈት የማይፈልግ መሆኑ ነው። የኢንዶስኮፒክ ሕክምና የሚሰራው በአጠቃላይ ማደንዘዣ በመጠቀም ነው። በዚህ ዘዴ በኤንዶስኮፒ እገዛ የላይኛው የሽንት ቧንቧ ወደ የሽንት ፊኛ የሚገባበት አካባቢ ይወጋል። በመርፌ ባልኪኝግ ዕቃ መውጋት የላይኛው የሽንት ቧንቧ መግቢያ ላይ ያለውን ተቃውሞ ከፍ ያደርገዋል ይህም ሽንት ተመልሶ ወደ ላይኛው የሽንት ቧንቧ እንዳይፈስ ይከላከላል። በዚህ ዘዴ የኋላ ፍሰትን የማስቀረት የስኬት መጠኑ ወደ 85 እስከ 90% ገደማ ነው። ደረጃው ገና በሆነ ቪዩአር የኢንዶስኮፒክ ሕክምና አንቲባዮቲኮችን ለረጅም ጊዜ ከመጠቀም እና ከቪዩአር ጋር ለዓመታት የመኖርን ጭንቀት ስለሚያስወግድ ምቹ የሕክምና አማራጭ ነው። ክትትል:- ቪዩአር ላለባቸው ሕፃናት በሙሉ በሃኪም ምክር መሰረት በመደበኛነት የቁመት ፣ ክብደት ፣ የደም ግፊት ፣ የሽንት አናሊሲስ እና ሌሎች ምርመራዎች ክትትል ሊደረግባቸው ይገባል።
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ህመምተኛ ሐኪም ማማከር ያለበት መቼ ነው?
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ላለባቸው ሕፃናት ሐኪም ወዲያውኑ መማከር ያለባቸው ጊዜያት:-
- የማያቋርጥ ትኩሳት ፣ ብርድ ብርድ ማለት ፣ በሽንት ጊዜ ህመም ወይም ማቃጠል ፣ መጥፎ ጠረን ያለው ሽንት ወይም በሽንት ውስጥ ደም መኖር
- ፈሳሽ እና መድሃኒት እንዳይወስዱ የሚከለክል ማቅለሽለሽ ወይም ማስ ታወክ
- ደካማ በሆነ የፈሳሽ አወሳሰድም ሆነ በማስመለስ ምክንያት የሚከሰት ድርቀት
- በታችኛው ጀርባ ወይም ሆድ ላይ ህመም
- መነጫነጭ፣የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ማደግ አለመቻል ወይም የልጅ ደህና አለመሆን